ዘኍል 27:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ሙሴ እጆቹን በኢያሱ ራስ ላይ ጭኖ ከዚያ በኋላ የእርሱ ተተኪ መሆኑን በግልጥ አስታወቀ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት ባዘዘው መሠረት እጁን በራሱ ላይ ጭኖ ሾመው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም በሙሴ እንደ ተናገረ፥ እጁን በእርሱ ላይ ጫነበት፥ አዘዘውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ሙሴን እንደ አዘዘው፥ እጁን በላዩ ጫነበትና፥ ሾመው፤ አዘዘውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም በሙሴ እንደ ተናገረ፥ እጁን በላዩ ጫነበት፥ አዘዘውም። |
“ከዚህም ቀጥሎ ኢያሱን እንዲህ ስል መከርኩት፤ ‘እግዚአብሔር አምላካችሁ ሲሖንና ዖግ ተብለው በሚጠሩት በሁለት ነገሥታት ያደረገውን በዐይናችሁ አይታችኋል፤ ምድሩን በምትወርሱበት በማንኛውም ሕዝብ ላይ ይህንኑ ተመሳሳይ ድርጊት ይደግመዋል።
ይልቅስ ለኢያሱ አስፈላጊውን መመሪያ ስጠው፤ በማበረታታትም አጠንክረው፤ ሕዝቡ ተሻግረው ይህችን የምታያትን ምድር ይወርሱ ዘንድ የሚመራቸው እርሱ ነው።’
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር የነዌን ልጅ ኢያሱን እንዲህ ሲል አዘዘው፦ “በርታ ደፋርም ሁን፤ እኔ ልሰጣቸው በመሐላ ቃል ወደገባሁላቸው ምድር የእስራኤልን ሕዝብ መርተህ ታገባለህ፤ እኔም ከአንተ ጋር እሆናለሁ።”
ሙሴ የእርሱ ተተኪ እንዲሆን እጆቹን በመጫን ሹሞት ስለ ነበር የነዌ ልጅ ኢያሱ በጥበብ የተሞላ ሆነ፤ የእስራኤልም ሕዝብ ለኢያሱ ታዘዘለት፤ እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት የሰጣቸውንም ትእዛዝ ጠበቁ።