ዘዳግም 34:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 ሙሴ የእርሱ ተተኪ እንዲሆን እጆቹን በመጫን ሹሞት ስለ ነበር የነዌ ልጅ ኢያሱ በጥበብ የተሞላ ሆነ፤ የእስራኤልም ሕዝብ ለኢያሱ ታዘዘለት፤ እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት የሰጣቸውንም ትእዛዝ ጠበቁ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 ሙሴ እጆቹን ጭኖበት ነበርና፣ የነዌ ልጅ ኢያሱ በጥበብ መንፈስ ተሞላ። ስለዚህ እስራኤላውያን አደመጡት፤ እግዚአብሔር ሙሴን አዝዞት የነበረውንም ሁሉ አደረጉ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 ሙሴም እጆቹን ስለ ጫነበት የነዌ ልጅ ኢያሱ የጥበብን መንፈስ ተሞላ፤ የእስራኤልም ልጆች ታዘዙለት፤ ሙሴንም ጌታ እንዳዘዘው አደረጉ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 ሙሴም እጆቹን ስለ ጫነበት የነዌ ልጅ ኢያሱ የጥበብን መንፈስ ተሞላ፤ የእስራኤልም ልጆች ታዘዙለት፤ እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 ሙሴም እጆቹን ስለ ጫነበት የነዌ ልጅ ኢያሱ የጥበብን መንፈስ ተሞላ፤ የእስራኤልም ልጆች ታዘዙለት፥ እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ። Ver Capítulo |