La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 21:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔርም ልመናቸውን ሰምቶ ስለ ረዳቸው ከነዓናውያንን ድል ነሥተው ያዙ፤ ስለዚህ እስራኤላውያን እነርሱንና ከተሞቻቸውን ፈጽመው ደመሰሱ፤ ፈጽሞ የተደመሰሱ መሆናቸውንም ለማመልከት ያን ስፍራ “ሖርማ” ብለው ሰየሙት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔርም የእስራኤልን ልመና ሰምቶ ከነዓናውያንን በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው፤ እነርሱም ሰዎቹንና ከተሞቻቸውን ፈጽመው ደመሰሱ፤ ከዚህ የተነሣም ስፍራው ሖርማ ተባለ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታም የእስራኤልን ድምፅ ሰማ፥ ከነዓናውያንንም አሳልፎ ሰጣቸው፤ እነርሱንም ከተሞቻቸውንም እርም ብለው አጠፉ፤ የዚያንም ስፍራ ስም ሔርማ ብለው ጠሩት።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ድምፅ ሰማ፤ ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ን​ንም አሳ​ልፎ በእ​ጃ​ቸው ሰጣ​ቸው፤ እነ​ር​ሱ​ንም፥ ከተ​ሞ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሕርም ብለው አጠ​ፉ​አ​ቸው፤ የዚ​ያን ስፍራ ስም “ሕርም” ብለው ጠሩት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔርም የእስራኤልን ድምፅ ሰማ፥ ከነዓናውያንንም አሳልፎ ሰጣቸው፤ እነርሱንም ከተሞቻቸውንም እርም ብለው አጠፉ፤ የዚያንም ስፍራ ስም ሔርማ ብለው ጠሩት።

Ver Capítulo



ዘኍል 21:3
11 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ሆይ! አንተ የምስኪኖችን ጸሎት ትሰማለህ፤ ልመናቸውንም አድምጠህ ታበረታታቸዋለህ።


የድኾችን ጸሎት ይሰማል፤ ልመናቸውንም አይንቅም።


ጩኸቴንና ልመናዬን ስለ ሰማ እግዚአብሔርን እወደዋለሁ።


በሚጠራኝም ጊዜ እሰማዋለሁ፤ በመከራው ጊዜ ከእርሱ ጋር እሆናለሁ፤ አድነዋለሁ፤ አከብረዋለሁም።


ከዚያም በኋላ በዚያ የሚኖሩት ዐማሌቃውያንና ከነዓናውያን በእነርሱ ላይ አደጋ ጥለው ድል አደረጉአቸው፤ እስከ ሖርማም ድረስ አሳደዱአቸው።


በነዚያ ኮረብታዎች ላይ የሚኖሩ አሞራውያንም መጥተው ተጋጠሙአችሁ፤ ሠራዊታቸውም እንደ ንብ መንጋ ግር ብለው መጥተው እስከ ሆርማ ድረስ አሳደዱአችሁ፤ ኮረብታማ በሆነችው በኤዶም አገርም ድል አደረጉአችሁ።


“እግዚአብሔር ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር የሚገኙትን ከተማዎች በጦርነት በምትይዝበት ጊዜ ግን በውስጣቸው የሚገኘውን ሰው ሁሉ ግደል።


ሖርማ፥ ዐራድ፥


ኤልቶላድ፥ ከሲል፥ ሖርማ፥


የይሁዳ ሕዝብ ከስምዖን ሕዝብ ጋር በአንድነት ዘምተው በጸፋት ከተማ ይኖሩ የነበሩትን ከነዓናውያንን ድል አደረጉ፤ ከተማይቱንም ፈጽመው ካጠፉአት በኋላ “ሖርማ” ብለው ሰየሙአት፤


በሖርማ፥ በቦርዓሻን፥ በዐታክና፥