Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘኍል 14:45 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

45 ከዚያም በኋላ በዚያ የሚኖሩት ዐማሌቃውያንና ከነዓናውያን በእነርሱ ላይ አደጋ ጥለው ድል አደረጉአቸው፤ እስከ ሖርማም ድረስ አሳደዱአቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

45 በዚህ ጊዜ በተራራማው አገር የሚኖሩት አማሌቃውያንና ከነዓናውያን ወርደው ወጓቸው፤ እስከ ሖርማ ድረስም አሳደዷቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

45 በዚያም ተራራ ላይ የተቀመጡ አማሌቃውያንና ከነዓናውያን ወረዱ፥ አሸንፈወዋቸውም እስከ ሔርማ ድረስ አሳደዱአቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

45 በዚ​ያም ተራራ ላይ የተ​ቀ​መጡ ዐማ​ሌ​ቃ​ዊና ከነ​ዓ​ናዊ ወረዱ፤ መት​ተ​ዋ​ቸ​ውም እስከ ኤርማ ድረስ አሳ​ደ​ዱ​አ​ቸው። ወደ ከተ​ማም ተመ​ለሱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

45 በዚያም ተራራ ላይ የተቀመጡ አማሌቃዊና ከነዓናዊ ወረዱ፥ መትተዋቸውም እስከ ሔርማ ድረስ አሳደዱአቸው።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 14:45
14 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔርም ልመናቸውን ሰምቶ ስለ ረዳቸው ከነዓናውያንን ድል ነሥተው ያዙ፤ ስለዚህ እስራኤላውያን እነርሱንና ከተሞቻቸውን ፈጽመው ደመሰሱ፤ ፈጽሞ የተደመሰሱ መሆናቸውንም ለማመልከት ያን ስፍራ “ሖርማ” ብለው ሰየሙት።


የይሁዳ ሕዝብ ከስምዖን ሕዝብ ጋር በአንድነት ዘምተው በጸፋት ከተማ ይኖሩ የነበሩትን ከነዓናውያንን ድል አደረጉ፤ ከተማይቱንም ፈጽመው ካጠፉአት በኋላ “ሖርማ” ብለው ሰየሙአት፤


በነዚያ ኮረብታዎች ላይ የሚኖሩ አሞራውያንም መጥተው ተጋጠሙአችሁ፤ ሠራዊታቸውም እንደ ንብ መንጋ ግር ብለው መጥተው እስከ ሆርማ ድረስ አሳደዱአችሁ፤ ኮረብታማ በሆነችው በኤዶም አገርም ድል አደረጉአችሁ።


ዐማሌቃውያንንና ከነዓናውያንን ፊት ለፊት ባያችሁ ጊዜ በጦርነት ትሞታላችሁ፤ እርሱን መከተል እምቢ ስላላችሁ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር አይሆንም።”


የዐይ ሰዎችም ወደ ሠላሳ ስድስት ያኽል ሰዎችን ገደሉባቸው፤ ከከተማይቱ ቅጥር በር ጀምሮ እስከ ሼባሪዎ ቊልቊለት ድረስ እየገደሉ አባረሩአቸው፤ የሕዝቡም ልብ ቀልጦ እንደ ውሃ ፈሰሰ።


ፈጣሪአቸው አሳልፎ ካልሰጣቸውና አምላካቸውም ካልተዋቸው በቀር እንዴት አንዱ ሺሁን ያሳድዳል? ወይም ሁለቱ ዐሥር ሺሁን ያባርራሉ?


እንዲህም አለ “የእግዚአብሔርን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ አድርጋችሁ ያዙ! እግዚአብሔር ዐማሌቃውያንን ለዘለዓለም ይዋጋቸዋል።”


ዐማሌቃውያን በኔጌብ ምድር የሚኖሩ ሲሆን፥ ሒታውያን፥ ኢያቡሳውያንና አሞራውያን በተራራማው አገር፥ ከነዓናውያን ደግሞ በዮርዳኖስ ወንዝ ዳርና በሜዲቴራኒያን በባሕር ዳር ይኖራሉ።”


እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤


በሖርማ፥ በቦርዓሻን፥ በዐታክና፥


ፍልስጥኤማውያንም አደጋ መጣል ጀመሩ፤ ከከባድ ጦርነት በኋላ እስራኤላውያንን ድል በመንሣት በጦር ሜዳ አራት ሺህ ሰው ገደሉባቸው፤


በዚያን ጊዜ ውስጥ ዳዊትና ተከታዮቹ በጌሪሹራውያን፥ በጌዛውያንና በአማሌቃውያን ላይ ዘመቱ፤ እነዚህም አገሮች ከቴሌኦም ጀምሮ ወደ ሱርና ወደ ምድረ ግብጽ የሚወስዱ እነርሱ የሚኖሩባቸው አገሮች ነበሩ።


የመዘዘውን ሰይፍ እንዲመልስ አድርገኸዋል፤ በጦርነትም አልረዳኸውም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios