የጸሩያ ልጅ ኢዮአብ የሕዝብ ቈጠራ ማድረግ ጀምሮ ሳይጨርስ ቀርቶ ነበር፤ በዚህ በሕዝብ ቈጠራ ምክንያት እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ ቀጥቶ ስለ ነበር የመጨረሻው ቊጥር በንጉሥ ዳዊት መንግሥት የታሪክ መዝገብ ውስጥ አልተመዘገበም ነበር።
ዘኍል 16:46 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴም አሮንን እንዲህ አለው፦ “የአንተን ጥና ወስደህ ከመሠዊያው የእሳት ፍም ጨምርበት፤ በፍሙም ላይ ዕጣን አድርግበት፤ ከዚያም ወደ ሕዝቡ በፍጥነት በመሄድ አስተስርይላቸው፤ ፍጠን! እነሆ፥ የእግዚአብሔር ቊጣ ከመገለጡ የተነሣ በሕዝቡ መካከል መቅሠፍት ጀምሮአል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሙሴ አሮንን፣ “ከእግዚአብሔር ዘንድ ቍጣ ወጥቶ መቅሠፍት ጀምሯልና ጥናውን ወስደህ ዕጣን በመጨመር ከመሠዊያው እሳት አድርግበት፤ ፈጥነህም ወደ ማኅበሩ ሄደህ አስተስርይላቸው” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም አሮንን እንዲህ አለው፦ “ጥናህን ውሰድ፥ ከመሠዊያውም ላይ እሳት አድርግበት፥ ዕጣንም ጨምርበት፥ ወደ ማኅበሩም ፈጥነህ ውሰደው አስተስርይላቸውም፤ ከጌታ ዘንድ ቁጣ ወጥቶአልና መቅሠፍት ጀምሮአል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም አሮንን፥ “ጥናህን ውሰድ፤ ከመሠዊያውም ላይ እሳት አድርግበት፤ ዕጣንም ጨምርበት፤ ወደ ማኅበሩም ፈጥነህ ውሰደው፤ አስተስርይላቸውም፤ ከእግዚአብሔር ፊት ቍጣ ወጥቶአልና፥ ሕዝቡንም ያጠፋቸው ዘንድ ጀምሮአል” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም አሮንን፦ ጥናህን ውሰድ፥ ከመሠዊያውም ላይ እሳት አድርግበት፥ ዕጣንም ጨምርበት፥ ወደ ማኅበሩም ፈጥነህ ውሰደው አስተስርይላቸውም፤ ከእግዚአብሔር ፊት ቁጣ ወጥቶአልና መቅሠፍት ጀምሮአል አለው። |
የጸሩያ ልጅ ኢዮአብ የሕዝብ ቈጠራ ማድረግ ጀምሮ ሳይጨርስ ቀርቶ ነበር፤ በዚህ በሕዝብ ቈጠራ ምክንያት እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ ቀጥቶ ስለ ነበር የመጨረሻው ቊጥር በንጉሥ ዳዊት መንግሥት የታሪክ መዝገብ ውስጥ አልተመዘገበም ነበር።
ከዚህ በኋላ ሙሴ አሮንን፥ እንዲሁም አልዓዛርና ኢታማር የተባሉትን ሁለቱን የአሮንን ልጆች እንዲህ አላቸው፤ “ለሐዘን ብላችሁ ጠጒራችሁን አትላጩ፤ ልብሳችሁንም አትቅደዱ፤ ይህን ብታደርጉ ግን ትሞታላችሁ፤ እግዚአብሔርም በሕዝቡ ላይ ቊጣውን ያወርዳል፤ ነገር ግን ወንድሞቻችሁ እስራኤላውያን ከእግዚአብሔር በተላከ እሳት ስለሞቱት ልጆች እንዲያለቅሱ ተፈቅዶላቸዋል።
እሳትም በድንገት ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ፥ በመሠዊያው ላይ የነበረውን መሥዋዕትና ስብ ሁሉ በላ፤ ሕዝቡ ሁሉ ይህን ባዩ ጊዜ እልል አሉ፤ በምድር ላይም በግንባራቸው ተደፍተው ሰገዱ።
እነሆ፥ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ ዳር እስከ ዳር ለእኔ ክብር ይሰጣሉ፤ በየትኛውም ስፍራ ለእኔ ዕጣን እያጠኑ ንጹሕ መሥዋዕት ያቀርቡልኛል፤ ሕዝቦችም ሁሉ ያከብሩኛል።
ነገር ግን ማንም ሰው ወደ ድንኳኑ በመቅረብ ቊጣዬን አነሣሥቶ የእስራኤልን ማኅበር እንዳያስፈጅ ሌዋውያን በድንኳኑ ዙሪያ ሰፍረው ይጠብቁት።”
ቊጣዬ በእስራኤል ሕዝብ ላይ እንደገና እንዳይገለጥ በተቀደሰው ስፍራና በመሠዊያው ላይ ያለውን የአገልግሎት ኀላፊነት የምትፈጽሙት እናንተና ልጆቻችሁ ብቻ ናችሁ።
ሰውየውና ሴቲቱ ወዳሉበት ድንኳን ገባ፤ ሁለቱንም በአንድነት በጦር ወግቶ ገደላቸው፤ በዚህም ዐይነት እስራኤላውያንን በማጥፋት ላይ የነበረው መቅሠፍት ቆመ፤
የእስራኤልን ሕዝብ ወክለው በመገናኛው ድንኳን ውስጥ እንዲያገለግሉና እስራኤላውያን ወደ ተቀደሰው ስፍራ በመቅረብ እንዳይቀሠፉ ይጠብቁአቸው ዘንድ፥ ሌዋውያንን ከእስራኤላውያን እንደ ስጦታ ተቀብዬ ለአሮንና ለልጆቹ ሰጥቻለሁ።”