ሦስት ኪሎ ተኩል የሚመዝን ከነሐስ የተሠራ ጦር የያዘና አዲስ ሰይፍ የታጠቀ ዩሽቢበኖብ ተብሎ የሚጠራ አንድ ኀያል ሰው ዳዊትን ለመግደል አስቦ ነበር፤
ዘኍል 13:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን በዚያች ምድር የሚኖሩ ሕዝብ እጅግ ብርቱዎች ናቸው፤ ከተሞቻቸውም ታላላቆችና የተመሸጉ ናቸው፤ ከዚህም ሁሉ በላይ እጅግ ግዙፋን የዐናቅ ዘሮች አይተናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ የሚኖሩት ሰዎች ግን ኀያላን ሲሆኑ፣ ከተሞቹም የተመሸጉና ትላልቅ ናቸው፤ እንዲያውም የዔናቅን ዝርያዎች በዚያ አይተናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን በምድሪቱ የሚኖሩ ሰዎች ኃያላን ናቸው፤ ከተሞቻቸውም የተመሸጉ እጅግም ሰፋፊዎች ናቸው፤ ደግሞም በዚያ የዔናቅን ልጆች አየን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን በምድሪቱ የሚኖሩ ሰዎች ኀያላን ናቸው፤ ከተሞቻቸውም የተመሸጉ፥ እጅግም የጸኑ ታላላቅ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን በምድሪቱ የሚኖሩ ሰዎች ኃያላን ናቸው። ከተሞቻቸውም የተመሸጉ እጅግም የጸኑ ናቸው፤ ደግሞም በዚያ የዔናቅን ልጆች አየን። |
ሦስት ኪሎ ተኩል የሚመዝን ከነሐስ የተሠራ ጦር የያዘና አዲስ ሰይፍ የታጠቀ ዩሽቢበኖብ ተብሎ የሚጠራ አንድ ኀያል ሰው ዳዊትን ለመግደል አስቦ ነበር፤
በዚያም ከኔፊሊም ወገን የሆኑትን የዐናቅን ዘሮች አይተናል፤ እኛ በእነርሱ ፊት ልክ እንደ ፌንጣ ያኽል ሆነን ነበር የታየነው፤ እነርሱም እንደዚያው አድርገው ሳይመለከቱን አይቀሩም” አሉ።
ታዲያ እዚያ የምንሄደው ለምንድን ነው? እንፈራለን፤ የላክናቸውም ሰዎች በዚያ የሚኖሩት ሁሉ ብርቱዎችና በቁመታቸውም ከእኛ ይበልጥ ረጃጅሞች መሆናቸውን፥ እንዲሁም ርዝመታቸው እስከ ሰማይ የሚደርስ የግንብ ቅጽሮች ባሉአቸው ከተሞች የሚኖሩ መሆናቸውን ነገሩን፤ እጅግ ግዙፋን የሆኑ የዔናቅ ልጆችንም አይተዋል።’
እነርሱም እንደ ዐናቃውያን ቁመተ ረጃጅሞች፥ ብርቱና ብዙ ሕዝብ ነበሩ፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ኀይል ዐሞናውያን ስለ ደመሰሱአቸው ምድራቸውን ወርሰው ራሳቸው ሰፍረውበት ነበር።
እነዚህም ሁሉ ከተሞች ከፍ ያለ ቁመት ባላቸው ቅጽሮች የተመሸጉ ነበሩ፤ የቅጽሮቹም በሮች በመወርወሪያ የሚዘጉ ነበሩ፤ ቅጽር የሌላቸው ብዙ መንደሮችም ነበሩ።
አሁን እንግዲህ እግዚአብሔር በዚያን ቀን በሰጠኝ ተስፋ መሠረት ይህን ኮረብታማ አገር ስጠኝ፤ ዐናቃውያን ከታላላቅ የተመሸጉ ከተሞች ጋር እንደ ነበሩ በዚያን ቀን ሰምተሃል፤ እግዚአብሔር እንዳለ እርሱ ከእኔ ጋር ሆኖ አሳድዳቸዋለሁ።