ዘኍል 1:46 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጠቅላላ የተቈጠሩት ስድስት መቶ ሦስት ሺህ አምስት መቶ ኀምሳ ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠቅላላ ቍጥራቸውም ስድስት መቶ ሦስት ሺሕ ዐምስት መቶ ዐምሳ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የተቈጠሩት ሁሉ ስድስት መቶ ሦስት ሺህ አምስት መቶ ኀምሳ ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተቈጠሩት ሁሉ ስድስት መቶ ሦስት ሺህ አምስት መቶ አምሳ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተቈጠሩት ሁሉ ስድስት መቶ ሦስት ሺህ አምስት መቶ አምሳ ነበሩ። |
ቀጥሎም እግዚአብሔር አብራምን ወደ ውጪ አወጣውና “ወደ ሰማይ ተመልከት፤ ከዋክብትን መቊጠር ትችል እንደሆን ሞክር፤ እንግዲህ የአንተም ዘሮች እንደዚህ ይበዛሉ” አለው።
እዚሁ ኑር፤ እኔም ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ እባርክሃለሁም፤ ይህን ምድር ለአንተና ለዘርህ እሰጣለሁ፤ በዚህ ዐይነት ለአባትህ ለአብርሃም የገባሁትን ቃል ኪዳን እፈጽማለሁ፤
ለውትድርና አገልግሎት ብቁ የሆኑትን ሰዎች ጠቅላላ ድምር ለዳዊት አስታወቀ፤ እነርሱም ከእስራኤል አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሺህ ሲሆኑ፥ ከይሁዳ ደግሞ አራት መቶ ሰባ ሺህ ነበሩ፤
ይህም በሕዝብ ቈጠራ ጊዜ የተመዘገቡት ሰዎች እያንዳንዳቸው በይፋ በታወቀው ሚዛን ልክ የከፈሉትን ድርሻ ጠቅላላ ድምር የሚያኽል ነበር፤ በሕዝብ ቈጠራ የተመዘገቡትም ኻያ ዓመት የሞላቸውና ከዚያም በላይ የሆኑት ስድስት መቶ ሦስት ሺህ አምስት መቶ ኀምሳ ወንዶች ነበሩ።
ሙሴም ለእግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “እነሆ፥ እኔ ስድስት መቶ ሺህ ሕዝብ በመምራት ላይ እገኛለሁ፤ ለአንድ ወር የሚበቃ ሥጋ ልትሰጣቸው ቃል ገብተሃል፤
ሁላችሁም ትሞታላችሁ፤ ሬሳችሁም በዚህ ምድረ በዳ ተበትኖ ይቀራል፤ በእኔ ላይ በማጒረምረማችሁ ምክንያት ከእናንተ መካከል ከኻያ ዓመት በላይ ዕድሜ ኖሮአችሁ የተቈጠራችሁት ሁሉ ከቶ ወደዚያች ምድር አትገቡም፤
እንደ ትቢያ ብዛት ያላቸውን የያዕቆብ ዘሮች ማን ሊቈጥር ይችላል ወይስ እንደ አዋራ ብናኝ ብዛት ያለውን የእስራኤልን ሩብ ብዛት ማን ሊገምት ይችላል? የጻድቃንን ሞት እንድሞት አድርገኝ መጨረሻዬንም እንደ እነርሱ አድርገው።”
የቀድሞ አባቶችህ ወደ ግብጽ በወረዱ ጊዜ ብዛታቸው ሰባ ብቻ ነበር፤ አሁን ግን እግዚአብሔር አምላክህ የአንተን ቊጥር ብዛት እንደ ሰማይ ከዋክብት አድርጎታል።