ዕዝራ እንዲህ ሲል እግዚአብሔርን አመሰገነ፦ “የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን! በኢየሩሳሌም ለሚሠራው ለእግዚአብሔር ቤት ንጉሠ ነገሥቱ ክብር ለመስጠት እንዲፈቅድ ያደረገው እርሱ ነው፤
ነህምያ 2:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለኢየሩሳሌም ስለማከናውነው ሥራ ሁሉ እግዚአብሔር ለእኔ የገለጠልኝን ምሥጢር ለማንም ሳልናገር ቈየሁ፤ ከዚያም በኋላ ከጓደኞቼ ጥቂቶቹን በማስከተል፥ በእኩለ ሌሊት ተነሥቼ ሄድኩ፤ የነበረን የጭነት እንስሳ እኔ የተቀመጥኩበት ብቻ ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከጥቂት ሰዎች ጋራ በሌሊት ወጣሁ። ለኢየሩሳሌም አደርገው ዘንድ አምላኬ በልቤ ያኖረውን ነገር ለማንም አልነገርሁም፤ ከተቀመጥሁበት እንስሳ በቀር ከእኔ ጋራ ሌሎች እንስሳት አልነበሩም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሌሊት ተነሣሁ፥ እኔና ከእኔም ጋር ጥቂት ሰዎች ነበሩ፤ ነገር ግን አምላኬ ለኢየሩሳሌም እንዳደርገው በልቤ ያስቀመጠውን ነገር ለማንም አልተናገርኩም። ተቀምጬበት ከነበረው እንስሳ በቀር ከእኔ ጋር ምንም እንስሳ አልነበረም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሌሊትም ተነሣሁ፤ ከእኔም ጋር ጥቂት ሰዎች ነበሩ፤ እግዚአብሔርም ለኢየሩሳሌም አደርገው ዘንድ በልቤ ያኖረውን ለማንም አላስታወቅሁም፤ ተቀምጬበት ከነበረው እንስሳ በቀር ከእኔ ጋር ምንም እንስሳ አልነበረም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሌሊትም ተነሣሁ፤ ከእኔም ጋር አያሌ ሰዎች ነበሩ፤ እግዚአብሔርም ለኢየሩሳሌም አደርገው ዘንድ በልቤ ያኖረውን ለማንም አላስታወቅሁም፤ ተቀምጬበት ከነበረው እንስሳ በቀር ከእኔ ጋር ምንም እንስሳ አልነበረም። |
ዕዝራ እንዲህ ሲል እግዚአብሔርን አመሰገነ፦ “የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን! በኢየሩሳሌም ለሚሠራው ለእግዚአብሔር ቤት ንጉሠ ነገሥቱ ክብር ለመስጠት እንዲፈቅድ ያደረገው እርሱ ነው፤
በሸለቆ ቅጽር በር ወጥቼ የዘንዶ ምንጭ ተብሎ የሚጠራውን ስፍራ በማለፍ፥ በስተ ደቡብ ወደሚገኘው የጒድፍ መጣያ ተብሎ ወደሚጠራው ስፍራ ሄድኩ፤ ጊዜውም ገና ሌሊት ነበር፤ በማልፍበትም ጊዜ የፈራረሱትን የከተማይቱን ቅጽሮችና በእሳት የወደሙትን የቅጽር በሮች ጐበኘሁ።
እነሆ ከዚህ ጊዜ በኋላ ከእስራኤል ሕዝብ ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነው፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፤ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ አምላካቸውም እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ፤
ከእነርሱ ጋር የዘለዓለም ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፤ ለእነርሱ መልካም ነገር ከማድረግም አላቋርጥም፤ በእውነት እንዲፈሩኝ አደርጋለሁ። ከዚያም በኋላ ፊታቸውን ከእኔ ወደ ሌላ አይመልሱም።
በሰው ላይ እምነትህን አትጣል፤ በቅርብ ወዳጅህም አትተማመን፤ አቅፈሃት ለምትተኛው ሚስትህ የምትናገረው ቃል እንኳ ጥንቃቄ የተሞላበት ይሁን።
ዕቅዱን እንዲፈጽሙ ይህን ሐሳብ በልባቸው ያኖረ እግዚአብሔር ነው፤ ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል እስኪፈጸም እነርሱ በአንድ ሐሳብ ይስማማሉ፤ የመንገሥ ሥልጣናቸውንም ለአውሬው ያስረክባሉ።
ጌዴዎንም ከአገልጋዮቹ ዐሥሩን ወስዶ እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ፤ ቤተሰቡንና የከተማይቱን ኗሪዎች ከመፍራቱም የተነሣ ይህን ያደረገው ቀን ሳይሆን በሌሊት ጨለማ ለብሶ ነበር።