Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ቆሮንቶስ 8:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 እኔ ለእናንተ የማስበውን ያኽል ቲቶም ለእናንተ ከልቡ እንዲያስብ ያደረገ አምላክ ይመስገን።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 እኔ ለእናንተ ያለኝን በጎ ሐሳብ በቲቶ ልብ ውስጥ ያኖረ አምላክ የተመሰገነ ይሁን፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ነገር ግን እኔ ለእናንተ ያለኝን በጎ ሐሳብ በቲቶ ልብ ውስጥ ያኖረ አምላክ የተመሰገነ ይሁን፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 በቲቶ ልብ ስለ እና​ንተ ያን መት​ጋት የሰጠ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​መ​ሰ​ገነ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ነገር ግን በቲቶ ልብ ስለ እናንተ ያንን ትጋት የሰጠ አምላክ ይመስገን፤

Ver Capítulo Copiar




2 ቆሮንቶስ 8:16
13 Referencias Cruzadas  

ንጉሥ ሕዝቅያስና ባለሟሎቹ የሆኑት ባለሥልጣኖች መጥተው፥ እጅግ የበዛውን የስጦታ ክምር ባዩ ጊዜ፥ እግዚአብሔርንና የእርሱ ወገኖች የሆኑትን የእስራኤልን ሕዝብ አመሰገኑ፤


ዕዝራ እንዲህ ሲል እግዚአብሔርን አመሰገነ፦ “የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን! በኢየሩሳሌም ለሚሠራው ለእግዚአብሔር ቤት ንጉሠ ነገሥቱ ክብር ለመስጠት እንዲፈቅድ ያደረገው እርሱ ነው፤


ለኢየሩሳሌም ስለማከናውነው ሥራ ሁሉ እግዚአብሔር ለእኔ የገለጠልኝን ምሥጢር ለማንም ሳልናገር ቈየሁ፤ ከዚያም በኋላ ከጓደኞቼ ጥቂቶቹን በማስከተል፥ በእኩለ ሌሊት ተነሥቼ ሄድኩ፤ የነበረን የጭነት እንስሳ እኔ የተቀመጥኩበት ብቻ ነበር፤


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እነሆ ከእስራኤል ሕዝብና ከይሁዳ ሕዝብ ጋር አዲስ ቃል ኪዳን የምገባበት ጊዜ ይመጣል፤


ከእነርሱ ጋር የዘለዓለም ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፤ ለእነርሱ መልካም ነገር ከማድረግም አላቋርጥም፤ በእውነት እንዲፈሩኝ አደርጋለሁ። ከዚያም በኋላ ፊታቸውን ከእኔ ወደ ሌላ አይመልሱም።


ስለዚህ ምንም እንኳ ለእናንተ ብጽፍ እኔ የጻፍኩላችሁ ስለ እኛ ያላችሁ ትጋት በእግዚአብሔር ፊት ለእናንተ ግልጥ እንዲሆን ብዬ ነው እንጂ በደል ስለ ሠራውና በደል ስለ ተፈጸመበት ሰው ብዬ አይደለም።


የተጽናናነውም በእርሱ መምጣት ብቻ ሳይሆን እናንተ እርሱን ያጽናናችሁት መሆኑን በመስማታችንም ጭምር ነው፤ ስለ እኔ ያላችሁን ናፍቆትና ሐዘን ጭንቀትም በነገረን ጊዜ ይበልጥ ደስ አለኝ።


ስለ ቲቶ ማወቅ ቢያስፈልግ እናንተን ለመርዳት አብሮኝ የሚሠራ የሥራ ጓደኛዬ ነው፤ ከእርሱ ጋር ስለሚመጡት ስለ ሌሎች ወንድሞች የሆነ እንደ ሆነ እነርሱ የአብያተ ክርስቲያን ተወካዮች ለክርስቶስ ክብር የቆሙ ናቸው።


ይህን ሥራ አስቀድሞ የጀመረው ቲቶ ስለ ነበረ አሁንም ይህንኑ የልግሥና ሥራችሁን ወደ ፍጻሜ እንዲያደርስ እርሱኑ ለምነነዋል።


ስለ እናንተ ሁኔታ ከልብ የሚያስብ ከጢሞቴዎስ በቀር ሌላ ሰው የለኝም።


በኢየሱስ በኩል እግዚአብሔር አብን እያመሰገናችሁ በቃልም ሆነ በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት፤ በእርሱም እግዚአብሔር አብን አመስግኑ።


ዕቅዱን እንዲፈጽሙ ይህን ሐሳብ በልባቸው ያኖረ እግዚአብሔር ነው፤ ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል እስኪፈጸም እነርሱ በአንድ ሐሳብ ይስማማሉ፤ የመንገሥ ሥልጣናቸውንም ለአውሬው ያስረክባሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos