Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 122:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 በኢየሩሳሌም ከተማ ሰላም እንዲሆን እንዲህ ብላችሁ ጸልዩ፤ “የሚወዱሽ ሁሉ ይበልጽጉ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 እንዲህ ብላችሁ ለኢየሩሳሌም ሰላም ጸልዩ፤ “የሚወድዱሽ ይለምልሙ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ለኢየሩሳሌም ሰላምን ለምኑ፥ አንተንም ለሚወድዱ መረጋጋት ይሁን።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 122:6
16 Referencias Cruzadas  

አምላክ ሆይ! ጽዮንን ለመርዳት፥ የኢየሩሳሌምን ቅጥሮች ለመገንባት እባክህ ፈቃድህ ይሁን።


ተማርካችሁ ሄዳችሁ እንድትኖሩባቸው ላደረግኋቸው ከተሞችም ዕድገት መልካም ነገርን ተመኙ፤ ስለ እነርሱም መልካም ኑሮ ወደ እኔ ጸልዩ፤ እነርሱ መልካም ኑሮ ቢኖሩ እናንተም መልካም ኑሮን ትኖራላችሁ።


የሚመርቁህን እመርቃለሁ፤ የሚረግሙህንም እረግማቸዋለሁ፤ በአንተም አማካይነት ሕዝቦች ሁሉ ይባረካሉ።”


እግዚአብሔር በባቢሎን ላሉት ሕዝብ እንዲህ ይላል፦ “እናንተ ከሞት የተረፋችሁ ሕዝቤ! ሳትዘገዩ ሂዱ! በሩቅ ሀገር ሆናችሁ እኔን እግዚአብሔርን አስታውሱ! ኢየሩሳሌምን በልባችሁ አስቡ!


ይህ ሕዝብ፥ ለመያዝ እንደ ተዘጋጁ ወንድ አንበሳና ሴት አንበሳ አድብቶአል፤ በተኛ ጊዜ ሊያስነሣው የሚደፍር ማነው? የሚመርቅህ የተመረቀ ይሁን፤ የሚረግምህም የተረገመ ይሁን።”


እኛ ወንድሞቻችንን ስለምንወድ ከሞት ወደ ሕይወት መሸጋገራችንን እናውቃለን። ፍቅር የሌለው ሰው በሞት ጥላ ውስጥ ይኖራል።


በሰላም ተሳስራችሁ ከእግዚአብሔር መንፈስ የሚገኘውን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ።


እኔም የምለምነው ሁሉም አንድ እንዲሆኑ ነው፤ እንዲሁም አባት ሆይ! አንተ በእኔ እንዳለህ፥ እኔም በአንተ እንዳለሁ፥ እነርሱም በእኛ እንዲኖሩ ነው፤ አንተ እንደ ላክኸኝም ዓለም እንዲያምን ነው።


የሰላም ጌታ ራሱ ሁልጊዜ በሁሉም ነገር ሰላምን ይስጣችሁ፤ ጌታ ከሁላችሁም ጋር ይሁን።


መልካሙንና ቅኑን ነገር አስተምራችኋለሁ እንጂ ስለ እናንተ መጸለይን በመተው እግዚአብሔርን እበድል ዘንድ ይህ ከእኔ ይራቅ።


መሪዎቹ መኖሪያቸውን በኢየሩሳሌም አደረጉ፤ ከሌላውም ሕዝብ መካከል ከየዐሥር ቤተሰብ አንዱ እጅ ቅድስት በሆነችው በኢየሩሳሌም ከተማ እንዲኖር በዕጣ ተመረጠ፤ የቀሩት ሰዎች ግን በሌሎች መንደሮችና ከተሞች ሁሉ ኑሮአቸውን መሠረቱ፤


ሕዝቡም በኢየሩሳሌም ውስጥ ለመኖር የበጎ ፈቃድ ዝንባሌ ያለውን ሰው ሁሉ አመሰገነ።


የአይሁድን ሕዝብ ለማስፈጀት በሱሳ ከተማ የተላለፈውን የዐዋጅ ቅጂም ለሀታክ ሰጠው፤ ይህንኑ የዐዋጅ ቅጂ ወስዶ ለአስቴር እንዲሰጣትና የሆነውንም ነገር ሁሉ እንዲገልጥላት፥ እንዲሁም ወደ ንጉሡ ዘንድ ገብታ ስለ ሕዝብዋ ምሕረትን እንድትለምን ይነግራት ዘንድ ሀታክን ለመነው።


ኢየሩሳሌምን እስኪመሠርታትና በምድር ሁሉ ዝነኛ ከተማ እስከሚያደርጋት ድረስ ሳታቋርጡ አሳስቡት።


የምትወዷት ሁሉ ከኢየሩሳሌም ጋር ደስ ይበላችሁ! ስለ እርስዋም ሐሴት አድርጉ! ያለቀሳችሁላት ሁሉ ስለ እርስዋ ተደሰቱ!


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios