ይህም ሁሉ በሕዝቡ መሪዎች ምክርና ትእዛዝ የተወሰነ ነበር፤ በሦስት ቀን ጊዜ ውስጥ ወደዚህ ስብሰባ መምጣት ያልቻለ ማንም ሰው ቢኖር ንብረቱ ሁሉ እንደሚወረስና ከምርኮ ከተመቱት ሰዎች ጉባኤ እንደሚወገድ ተነገረው።
ነህምያ 13:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሊቀ ካህናቱ ከኤልያሺብ ልጆች አንዱ ዮያዳዕ ነበር፤ ነገር ግን ከእርሱ ልጆች አንዱ የቤትሖሮን ከተማ ነዋሪ የሆነውን የሰንባላጥን ሴት ልጅ አግብቶ ነበር፤ ስለዚህም ዮያዳዕ ኢየሩሳሌምን ለቆ እንዲወጣ አደረግሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሊቀ ካህኑ ከኤልያሴብ ልጅ ከዮአዳ ልጆች አንዱ የሖሮናዊው የሰንባላጥ አማች ነበረ፤ እኔም ከአጠገቤ አባረርሁት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዋነኛውም ካህን ከኤልያሴብ ልጅ ከዮአዳ ልጆች አንዱ ለሖሮናዊው ለሰንበላጥ አማች ነበረ፥ ከእኔም ዘንድ አባረርሁት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዋነኛውም ካህን ከኤልያሴብ ልጅ ከዮዳሔ ልጆች አንዱ ለሐሮናዊው ለሰንባላጥ አማች ነበረ፤ ከእኔም ዘንድ አባረርሁት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዋነኛውም ካህን ከኤልያሴብ ልጅ ከዮአዳ ልጆች አንዱ ለሖሮናዊው ለሰንበላጥ አማች ነበረ፥ ከእኔም ዘንድ አባረርሁት። |
ይህም ሁሉ በሕዝቡ መሪዎች ምክርና ትእዛዝ የተወሰነ ነበር፤ በሦስት ቀን ጊዜ ውስጥ ወደዚህ ስብሰባ መምጣት ያልቻለ ማንም ሰው ቢኖር ንብረቱ ሁሉ እንደሚወረስና ከምርኮ ከተመቱት ሰዎች ጉባኤ እንደሚወገድ ተነገረው።
ኤልያሺብ፥ ዮያዳዕ፥ ዮናታንና ያዱዐ ተብለው የሚጠሩት ሊቃነ ካህናት በኖሩበት ዘመን የሌዋውያንና የካህናት ቤተሰብ አለቆች ተለይተው የሚታወቁበት መዝገብ ተዘጋጅቶ ነበር፤ ይህም መዝገብ የተዘጋጀው ዳርዮስ የፋርስ ንጉሠ ነገሥት በሆነበት ዘመን ነበር።
እነዚህንም ሰዎች ገሠጽኳቸው፤ ረገምኳቸውም፤ ደብድቤም ጠጒራቸውን ነጨሁ፤ ከዚህም በኋላ እነርሱም ሆኑ ልጆቻቸው ከባዕዳን ሕዝብ ጋር ጋብቻ እንዳይፈጽሙ በእግዚአብሔር ስም አስማልኳቸው።
ነገር ግን የቤትሖሮን ከተማ ነዋሪ የሆነው ሰንባላጥና የዐሞን ክፍለ ሀገር ባለሥልጣን የሆነው ጦቢያ ለእስራኤል ሕዝብ ደኅንነት መልካም ነገር የሚሠራ ሰው መምጣቱን ሰምተው እጅግ ተቈጡ።
ነገር ግን ሰንባላጥና ጦቢያ እንዲሁም ጌሼም ተብሎ የሚጠራው አንድ የዐረብ ተወላጅ እኛ ያወጣነውን የሥራ ዕቅድ በሰሙ ጊዜ በእኛ ላይ እየዘበቱ በመሳቅ “ይህ የምትሠሩት ሥራ ምንድን ነው? ወይስ በንጉሠ ነገሥቱ ላይ ማመፅ ትፈልጋላችሁን?” ሲሉ ጠየቁን።
የከተማይቱ ቅጽር እንደገና የተሠራው በዚህ ዐይነት ነበር፦ ሊቀ ካህናቱ ኤልያሺብና የእርሱ ሥራ ባልደረቦች የሆኑት ካህናት “የበጎች በር” ተብሎ የሚጠራውን ቅጽር በር እንደገና ሠርተው ለእግዚአብሔር የተለየ አደረጉት፤ በሮችንም አበጁለት፤ ቅጽሩንም “መቶ” ተብሎ እስከሚጠራው የመጠበቂያ ግንብና “ሐናንኤል” ተብሎ እስከሚጠራው ሌላ የመጠበቂያ ግንብ ድረስ ለእግዚአብሔር የተለየ አደረጉት።