Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ነህምያ 12:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ኢያሱ ዮያቂምን ወለደ፤ ዮያቂም ኤልያሺብን ወለደ፤ ኤልያሺብ ዮያዳዕን ወለደ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ኢያሱ ዮአቂምን ወለደ፤ ዮአቂም ኤልያሴብን ወለደ፤ ኤልያሴብ ዮአዳን ወለደ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ኢያሱም ዮያቂምን ወለደ፥ ዮያቂም ኤልያሺብን ወለደ፥ ኤልያሺብ ዮያዳዕን ወለደ፥

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ኢያ​ሱም ዮአ​ቂ​ምን ወለደ፤ ዮአ​ቂ​ምም ኤሊ​ያ​ሴ​ብን ወለደ፤ ኤሊ​ያ​ሴ​ብም ዮሐ​ዳን ወለደ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ኢያሱም ዮአቂምን ወለደ፥ ዮአቂምም ኤልያሴብን ወለደ፥ ኤልያሴብም ዮአዳን ወለደ፥

Ver Capítulo Copiar




ነህምያ 12:10
11 Referencias Cruzadas  

ዮያዳዕ ዮናታንን ወለደ፤ ዮናታን ያዱዓን ወለደ።


ኤልያሺብ፥ ዮያዳዕ፥ ዮናታንና ያዱዐ ተብለው የሚጠሩት ሊቃነ ካህናት በኖሩበት ዘመን የሌዋውያንና የካህናት ቤተሰብ አለቆች ተለይተው የሚታወቁበት መዝገብ ተዘጋጅቶ ነበር፤ ይህም መዝገብ የተዘጋጀው ዳርዮስ የፋርስ ንጉሠ ነገሥት በሆነበት ዘመን ነበር።


እነዚህም የኢዮጼዴቅ የልጅ ልጅ የሆነው የኢያሱ ልጅ ዮያቂም፥ አገረ ገዢው ነህምያ ካህኑና የሕግ ሊቁ ዕዝራ በነበሩበት ዘመን የተመደቡ አገልጋዮች ነበሩ።


ባቅቡቅያ፥ ዑኖና ሌሎችም ሌዋውያን ወንድሞቻቸው ከእነርሱ ጋር በመቀባበል ይዘምሩ ነበር።


ከሊቀ ካህናቱ ከኤልያሺብ ልጆች አንዱ ዮያዳዕ ነበር፤ ነገር ግን ከእርሱ ልጆች አንዱ የቤትሖሮን ከተማ ነዋሪ የሆነውን የሰንባላጥን ሴት ልጅ አግብቶ ነበር፤ ስለዚህም ዮያዳዕ ኢየሩሳሌምን ለቆ እንዲወጣ አደረግሁ።


የቤተ መቅደስ ዕቃ ግምጃ ቤት ኀላፊ የሆነው ካህኑ ኤልያሺብ ለረጅም ጊዜ ከጦቢያ ጋር የጠበቀ ግንኙነት ነበረው፤


ወደ ኢየሩሳሌም ተመለስኩ፤ እዚያም እንደ ደረስኩ ኤልያሺብ ለጦቢያ በቤተ መቅደሱ ግቢ ውስጥ አንድ መኖሪያ ክፍል የፈቀደለት መሆኑን ሰማሁ፤


የከተማይቱ ቅጽር እንደገና የተሠራው በዚህ ዐይነት ነበር፦ ሊቀ ካህናቱ ኤልያሺብና የእርሱ ሥራ ባልደረቦች የሆኑት ካህናት “የበጎች በር” ተብሎ የሚጠራውን ቅጽር በር እንደገና ሠርተው ለእግዚአብሔር የተለየ አደረጉት፤ በሮችንም አበጁለት፤ ቅጽሩንም “መቶ” ተብሎ እስከሚጠራው የመጠበቂያ ግንብና “ሐናንኤል” ተብሎ እስከሚጠራው ሌላ የመጠበቂያ ግንብ ድረስ ለእግዚአብሔር የተለየ አደረጉት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos