ናሆም 3:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእሳት ትቃጠያለሽ ሕዝብሽም በጦርነት ማለቁ አይቀርም፥ በአንበጣ እንደ ተበላ ሰብል ትጠፊያለሽ፤ ስለዚህ እንደ አንበጣና እንደ ኲብኲባ ተባዙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ እሳት ይበላሻል፤ ሰይፍ ይቈርጥሻል፤ እንደ ኵብኵባም ይግጥሻል። እንደ ኵብኵባ ርቢ፤ እንደ አንበጣም ተባዢ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያ እሳት ይበላሻል፥ ሰይፍ ይቆርጥሻል፥ እንደ አንበጣ ይበላሻል። እንደ አንበጣ ብዢ፥ እንደ አንበጣም ተባዢ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያ እሳት ይበላሻል፥ ሰይፍ ያጠፋሻል፥ እንደ ደጎብያ ይበላሻል፣ እንደ ደጎብያ ብዢ፥ እንደ አንበጣም ተባዢ። |
የሠራዊት አምላክ በባቢሎን ላይ ብዛቱ እንደ አንበጣ መንጋ የሆነ ሠራዊት እንደሚያመጣባት በስሙ ምሎአል፤ ያም ሠራዊት ድልን በመቀዳጀት ይደነፋል።
ከተምች መንጋ የተረፈውን ሰብል፥ የሚርመሰመስ የአንበጣ መንጋ በላው፤ ከዚያ የተረፈውን እንደ ውሽንፍር የሚገርፍ የአንበጣ መንጋ አጠፋው፤ ከዚያም የተረፈውን ኲብኲባ በላው።
ለዘመናት እንደ ትልቅ ሠራዊት የላክሁባችሁ እንደ ውሽንፍር የሚገርፉ አንበጦች፥ ኲብኲባዎች፥ ተምቾችና የሚርመሰመሱ አንበጦች የፈጁባችሁን ሰብል እተካላችኋለሁ።
ጌታ እግዚአብሔር ይህን ራእይ አሳየኝ፤ እነሆ የንጉሡ የመከር እህል ከታጨደ በኋላ እንደገና ገቦ ሆኖ በበቀለው እህል ላይ እግዚአብሔር የአንበጣ መንጋ እንዲፈለፈል አደረገ፤
ነነዌ ሆይ! በአንቺ ላይ ተነሥቼአለሁ ይላል የሠራዊት አምላክ፤ ሠረገሎችሽንም አቃጥላለሁ፤ ደቦሎችሽንም ሰይፍ ይበላቸዋል፤ በምድር ላይ በአንቺ ተጠቂ የሚሆን እንዳይኖር አደርጋለሁ፤ የመልእክተኞችሽም ድምፅ ከእንግዲህ ወዲያ አይሰማም።