Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ናሆም 3:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ነጋዴዎችሽ ከሰማይ ከዋክብት ይበልጥ በዝተዋል፤ ነገር ግን እንደ አንበጣ ምድሪቱን ግጠው በረው ይሄዳሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ከሰማይ ከዋክብት እስኪበልጡ ድረስ፣ የነጋዴዎችሽን ቍጥር አበዛሽ፤ ምድሪቱን ግን እንደ አንበጣ ግጠው አሟጠጡ፤ ከዚያ በርረው ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ነጋዴዎችሽን ከሰማይ ከዋክብት ይልቅ አበዛሽ፤ አንበጣ ተዘረጋና በረረ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ነጋዴዎችሽን ከሰማይ ከዋክብት ይልቅ አበዛሽ፣ ደጎብያ ተዘረጋ፥ በረረም።

Ver Capítulo Copiar




ናሆም 3:16
7 Referencias Cruzadas  

ቀጥሎም እግዚአብሔር አብራምን ወደ ውጪ አወጣውና “ወደ ሰማይ ተመልከት፤ ከዋክብትን መቊጠር ትችል እንደሆን ሞክር፤ እንግዲህ የአንተም ዘሮች እንደዚህ ይበዛሉ” አለው።


እኔም ዘርህን እንደ ሰማይ ከዋክብትና እንደ ባሕር ዳር አሸዋ አበዛዋለሁ፤ ዘሮችህም ጠላቶቻቸውን ድል ነሥተው ከተሞቻቸውን ይይዛሉ።


ብዛታቸው እንደ ሰማይ ከዋክብት የሆኑ ልጆችን ሰጠሃቸው፥ ለቀድሞ አባቶቻቸው ትሰጣቸው ዘንድ ቃል የገባህላቸውን ምድር፥ በድል አድራጊነት እንዲይዙ ፈቀድክላቸው።


እርሱ ባዘዘው መሠረት ሊቈጠር የማይችል የአንበጣና የኲብኲባ መንጋ መጣ።


ዘውድን ታቀዳጅ በነበረችው ከተማ፥ ልዑላን የሆኑና በዓለም የተከበሩ ነጋዴዎች በነበርዋት በጢሮስ ላይ ይህን ሁሉ ያቀደ ማነው?


ስለዚህ የአገልጋዬን የዳዊትን ዘርና ከሌዊ ወገን የሆኑትን ካህናት ቊጥር አበዛለሁ፤ ብዛታቸውም ሊቈጠር እንደማይችል እንደ ባሕር አሸዋና እንደ ሰማይ ከዋክብት ይሆናል።”


ከተምች መንጋ የተረፈውን ሰብል፥ የሚርመሰመስ የአንበጣ መንጋ በላው፤ ከዚያ የተረፈውን እንደ ውሽንፍር የሚገርፍ የአንበጣ መንጋ አጠፋው፤ ከዚያም የተረፈውን ኲብኲባ በላው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos