አዛሄልም “ጌታዬ ስለምን ታለቅሳለህ?” ሲል ጠየቀው። ኤልሳዕም “በእስራኤል ሕዝብ ላይ የምትፈጽመውን አሠቃቂ ነገር ስለማውቅ ነው፤ ምሽጎቻቸውን በእሳት ታቃጥላለህ፤ ምርጥ የሆኑ ወጣቶቻቸውን ታርዳለህ፤ ሕፃናታቸውን በድንጋይ ላይ ትፈጠፍጣለህ፤ እርጉዞች የሆኑ ሴቶቻቸውንም ሆድ ትሰነጥቃለህ” ሲል መለሰለት።
ናሆም 3:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም ሁሉ ሆኖ የቴብስ ከተማ በጠላት ተይዛ ሕዝቦችዋ ተማርከዋል፤ ሕፃናትዋም በድንጋይ ተፈጥፍጠው በየመንገዱ ወድቀዋል፤ በልዑላኑ ላይ ዕጣ ተጣጣሉ፤ ሹማምንቱንም በሰንሰለት አሰሩአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁን እንጂ በምርኮ ተወሰደች፤ ተሰድዳም ሄደች። በየመንገዱ ማእዘን ላይ፣ ሕፃናቷ ተፈጠፈጡ፤ በመሳፍንቷ ላይ ዕጣ ተጣለ፤ ታላላቅ ሰዎቿ ሁሉ በሰንሰለት ታሰሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሆኖም ግን ተማርካ ተወሰደች፤ ሕፃናቶችዋ በመንገዶች ሁሉ ራስ ላይ ተፈጠፈጡ፤ በከበርቴዎችዋ ላይ ዕጣ ተጣጣሉ፥ ታላላቆችዋም ሁሉ በሰንሰለት ታሰሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስዋ ግን ተማርካ ፈለሰች፣ ሕፃናቶችዋ በመንገድ ሁሉ ራስ ላይ ተፈጠፈጡ፣ በከበርቴዎችዋም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ፥ ታላላቆችዋም ሁሉ በሰንሰለት ታሰሩ። |
አዛሄልም “ጌታዬ ስለምን ታለቅሳለህ?” ሲል ጠየቀው። ኤልሳዕም “በእስራኤል ሕዝብ ላይ የምትፈጽመውን አሠቃቂ ነገር ስለማውቅ ነው፤ ምሽጎቻቸውን በእሳት ታቃጥላለህ፤ ምርጥ የሆኑ ወጣቶቻቸውን ታርዳለህ፤ ሕፃናታቸውን በድንጋይ ላይ ትፈጠፍጣለህ፤ እርጉዞች የሆኑ ሴቶቻቸውንም ሆድ ትሰነጥቃለህ” ሲል መለሰለት።
የአሦር ንጉሠ ነገሥት ለግብጻውያን ኀፍረት ይሆን ዘንድ መቀመጫዎቻቸው ሳይሸፈኑ ወጣቶችም ሆኑ ሽማግሌዎች ዕራቊታቸውንና ባዶ እግራቸውን ሆነው ግብጾችንና ኢትዮጵያውያንን በምርኮ ይመራቸዋል።
እናንተ ሌሊቱን በሙሉ ተነሥታችሁ ጩኹ፤ በልባችሁ የሚሰማችሁን ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ፊት አቅርቡ፤ በየመንገዱ ማእዘን በራብ ለሚዝለፈለፉ ልጆቻችሁ ሕይወት በጸሎት እጆቻችሁን ወደ እግዚአብሔር አንሡ።
ሰማርያ በእኔ ላይ በማመፅዋ በሠራችው በደል ተጠያቂ ትሆናለች፤ ሕዝብዋም በጦርነት ይሞታሉ፤ ሕፃናት በምድር ላይ ይፈጠፈጣሉ፤ እርጉዞችም ሆዳቸው ይሰነጠቃል።”
የማረኩአቸውን ሕዝቤንም ለመከፋፈል ዕጣ ተጣጥለዋል፤ አመንዝራ ሴቶችን ለማግኘት ወንዶች ልጆችን ሰጡ፤ ወይን ጠጅ ለመጠጣትም ሴቶች ልጆችን ባሪያ አድርገው ሸጡ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የዐሞን ሕዝብ ደጋግመው ስለ ሠሩት ኃጢአት ያለ ጥርጥር እቀጣቸዋለሁ፤ እነርሱ ግዛት ለማስፋፋት ባደረጉት ወረራ በገለዓድ የሚኖሩትን እርጉዞች ሴቶች እንኳ ሆዳቸውን ቀደዋል።
ጠላቶቻቸው በሮቻቸውን ሰባብረው፥ ሀብታቸውን ሁሉ በዘረፉበት ቀን፥ አንተ በዳር ቆመህ ትመለከት ነበር፤ አንተ እኮ ኢየሩሳሌምን በዕጣ ከተከፋፈሉአት ሰዎች በምንም አትሻልም።