ይሁዳ እንደ ደቦል አንበሳ ነው፤ ልጄ መብል የሚሆነውን አድኖ፥ ወደ ዋሻው ይመለሳል፤ እንደ አንበሳ ተዝናንቶ ይተኛል፤ ሊቀሰቅሰው የሚደፍር ማነው?
ሚክያስ 5:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንበሳ በብዙ የዱር አራዊት መካከል፥ የአንበሳ ደቦልም በበግ መንጋዎች መካከል ዘለው ጉብ እያሉባቸውና እየቦጫጨቁ በሚሄዱበት ጊዜ ለአራዊቱ ምንም ረዳት አይገኝላቸውም፤ ከሞት የተረፉትንም የያዕቆብን ልጆች በብዙ ሕዝቦች መካከል እንደዚሁ ያደርጋሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዱር አራዊት መካከል እንዳለ አንበሳ፣ በእግሩ እየጨፈላለቀ እንደሚሄድ፣ የሰበረውን ማንም ሊነጥቀው እንደማይችል፣ በበግ መንጋ መካከል እንዳለ፣ እንደ ደቦል አንበሳ ሁሉ፣ የያዕቆብም ትሩፍ፣ በአሕዛብ ዘንድ፣ በብዙም ሕዝብ መካከል እንደዚሁ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እጅህ በጠላቶችህ ላይ ትነሣለች፥ ጠላቶችህም ሁሉ ይጠፋሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዱር አራዊትም መካከል እንዳለ አንበሳ፥ በበጎች መንጋም መካከል አልፎ እንደሚረግጥ፥ የሚታደግም ሳይኖር እንደሚነጥቅ እንደ አንበሳ ደቦል፥ እንዲሁ የያዕቆብ ቅሬታ በአሕዛብና በብዙ ወገኖች መካከል ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዱር አራዊትም መካከል እንዳለ አንበሳ፥ በበጎች መንጋም መካከል አልፎ እንደሚረግጥ፥ የሚታደግም ሳይኖር እንደሚነጥቅ እንደ አንበሳ ደቦል፥ እንዲሁ የያዕቆብ ቅሬታ በአሕዛብና በብዙ ወገኖች መካከል ይሆናል። |
ይሁዳ እንደ ደቦል አንበሳ ነው፤ ልጄ መብል የሚሆነውን አድኖ፥ ወደ ዋሻው ይመለሳል፤ እንደ አንበሳ ተዝናንቶ ይተኛል፤ ሊቀሰቅሰው የሚደፍር ማነው?
ስለዚህም ከየስፍራው የማገዶ እንጨት መሰብሰብም ሆነ፥ ከየጫካውም ዛፍ መቊረጥ አያስፈልጋቸውም፤ ምክንያቱም ወድቆ የቀረውን የጦር መሣሪያ ሁሉ ሰብስበው ማንደድ ይችላሉ፤ ቀድሞ የበዘበዙአቸውንና የዘረፉአቸውን አሁን በተራቸው መበዝበዝና መዝረፍ ይችላሉ፤” ልዑል እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአል።
ከዚህ የተነሣ እስራኤልን እንደ አንበሳ፥ ይሁዳንም እንደ ደቦል አንበሳ በመሆን ሰባብሬአቸው እሄዳለሁ፤ ነጥቄ እወስዳቸዋለሁ፤ ማንም ሊያድናቸው አይችልም።
“የእስራኤል ሕዝብ! በጎች በበረት፥ የበግ መንጋም በማሰማሪያ ቦታ እንደሚሰበሰብ በእርግጥ ከእስራኤል ሕዝብ የተረፉትን በአንድነት እሰበስባለሁ፤ ምድሪቱም በሕዝብ የተሞላች ትሆናለች” ይላል እግዚአብሔር።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እናንተ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ሆይ! ሂዱና ጠላቶቻችሁን እንደ እህል አበራዩ! ቀንዱ ብረት፥ ሰኮናው ነሐስ እንደ ሆነ በሬ ብርቱ አደርጋችኋለሁ፤ ብዙ መንግሥታትን ትደመስሳላችሁ፤ እነርሱ በግፍ የሰበሰቡትን ሀብትና ንብረት ሁሉ ለመላው ዓለም ጌታ ለእኔ ለእግዚአብሔር አምጥታችሁ ታቀርባላችሁ።”
አንካሶች ተርፈው እንዲኖሩ አደርጋለሁ፤ ተጥለው የነበሩትን ብርቱ ሕዝብ አደርጋቸዋለሁ፤ እኔም በጽዮን ተራራ ላይ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም በእነርሱ ላይ እነግሣለሁ።”
ስለዚህ እናቱ እርሱን እስከምትወልድበት ጊዜ ድረስ እግዚአብሔር ሕዝቡን ይተዋቸዋል፤ ከዚህ በኋላ በስደት ላይ ያሉት ወገኖቹ ተመልሰው ከወገኖቻቸው ጋር ይቀላቀላሉ።
ኃጢአትን ይቅር የሚል፥ በቀሪውም ሕዝቡ ላይ በደልን የማይቈጥር እንደ አንተ ያለ አምላክ ማን ነው? ምሕረት ማድረግ ስለሚያስደስትህ ቊጣህ ለዘለዓለም የሚቈይ አይደለም።
የይሁዳ ሕዝብ ጠላቶቻቸውን ረግጠው ከመንገድ ጭቃ ጋር እንደሚለውሱ እንደ ብርቱ ጦረኞች ይሆናሉ፤ እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር ስለ ሆነ በርትተው በመዋጋት ፈረሰኞችን ሳይቀር ድል ይነሣሉ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔም ከእንግዲህ ወዲህ በምድር ላይ ለሚኖር ለማንም ሰው ርኅራኄ አላደርግም፤ እኔ ራሴ እያንዳንዱን ሰው ለጐረቤቱና ለንጉሡ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እነርሱ ምድሪቱን ያጠፋሉ፤ እኔም ከእነርሱ እጅ አልታደጋቸውም።”
በዚያን ቀን ኢየሩሳሌምን ለአሕዛብ ሁሉ እንደ ከባድ ድንጋይ አደርጋታለሁ፤ እርስዋን ለማንሣት የሚሞክር ሁሉ ራሱን ይጐዳል፤ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ እርስዋን ለማጥቃት ተባብረው ይመጣሉ፤
ግብጻውያንም በዓሉን ለማክበር ወደ ኢየሩሳሌም ወጥተው በእግዚአብሔር ፊት መቅረብ ባይፈልጉ፥ “ወደ ኢየሩሳሌም ወጥተን የዳስ በዓል አናከብርም” በሚሉ መንግሥታት ላይ የሚደርሰው ቀሣፊ በሽታ ይመጣባቸዋል።
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ይከላከልላቸዋል፤ እነርሱም ጠላቶቻቸውን ይደመስሳሉ፤ የጠላትንም የወንጭፍ ድንጋይ ይረጋግጣሉ፤ የወይን ጠጅ ጠጥቶ እንደ ሰከረ ሰው ይጮኻሉ፤ የጠላቶቻቸውም ደም የመሥዋዕት ደም በሳሕን ሞልቶ በመሠዊያ ላይ እንደሚፈስስ ይፈስሳል።
ይህ ሕዝብ፥ ለመያዝ እንደ ተዘጋጁ ወንድ አንበሳና ሴት አንበሳ አድብቶአል፤ በተኛ ጊዜ ሊያስነሣው የሚደፍር ማነው? የሚመርቅህ የተመረቀ ይሁን፤ የሚረግምህም የተረገመ ይሁን።”
ነገር ግን አይሁድ በተቃወሙትና በሰደቡት ጊዜ የልብሱን ትቢያ አራግፎ “እንግዲህ ቢፈረድባችሁ በራሳችሁ ጥፋት ነው! እኔ ኀላፊነት የለብኝም፤ ከእንግዲህ ወዲህ ወደ አሕዛብ እሄዳለሁ!” አላቸው።
ያንን የሚናገረውን አንቀበልም እንዳትሉ ተጠንቀቁ፤ እነዚያ እግዚአብሔር በሰው አማካይነት ከምድር ሲናገራቸው አንሰማም ያሉት ካላመለጡ፥ ታዲያ እኛ ከሰማይ የሚናገረንን ባንቀበል እንዴት እናመልጣለን!
ታዲያ፥ እኛ ይህን ታላቅ መዳን ችላ የምንል ከሆንን እንዴት እናመልጣለን? ይህን መዳን በመጀመሪያ ያበሠረው ጌታ ራሱ ነው፤ ከእርሱ የሰሙትም ሰዎች ይህንኑ አረጋግጠውልናል።