ሚክያስ 3:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ ፍትሕን የምትጸየፉና ትክክለኛውን ነገር ሁሉ የምታጣምሙ የያዕቆብ ልጆች መሪዎች፥ የእስራኤል ሕዝብ አለቆች ይህን ስሙ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ የያዕቆብ ቤት መሪዎች፣ እናንተ የእስራኤል ቤት ገዦች፣ ፍትሕን የምትንቁ፣ ትክክለኛ የሆነውንም ነገር ሁሉ የምታጣምሙ፤ ስሙ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍትሕን የምትጠሉ፥ ትክክለኛውንም ነገር ሁሉ የምታጣምሙ እናንተ የያዕቆብ ቤት አለቆችና የእስራኤል ቤት ገዢዎች ሆይ፥ እባካችሁ ይህን ስሙ፦ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍርድን የምትጠሉ ቅን ነገርንም ሁሉ የምታጣምሙ እናንተ የያዕቆብ ቤት አለቆችና የእስራኤል ቤት ገዦች ሆይ፥ እባካችሁ ይህን ስሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፍርድን የምትጠሉ ቅን ነገርንም ሁሉ የምታጣምሙ እናንተ የያዕቆብ ቤት አለቆችና የእስራኤል ቤት ገዦች ሆይ፥ እባካችሁ ይህን ስሙ። |
እንግዲህ ሂድና የእስራኤልን ሕዝብ አለቆች ሁሉ በአንድነት ሰብስብ፤ የቀድሞ አባቶቻቸው የአብርሃም የይስሐቅና የያዕቆብ አምላክ እኔ እግዚአብሔር የተገለጥኩልህ መሆኔንም ንገራቸው፤ ወደ እነርሱ ወርጄ ግብጻውያን በእነርሱ ላይ ያደረሱባቸውን ግፍና ጭቈና መመልከቴን ንገራቸው።
መሪዎችሽ ዐመፀኞችና የሌቦች ግብረ አበሮች ሆኑ፤ እያንዳንዱ ሁልጊዜ ገጸ በረከትና ጉቦ ይቀበላል፤ አባትና እናት የሞቱባቸውን ልጆች መብት አይጠብቁም፤ ባሎቻቸው የሞቱባቸውንም ሴቶች አቤቱታ አይሰሙም።
እነርሱ እንደ ቅልብ ሰንጋ ወፍረዋል፤ ክፉ ሥራቸውም ገደብ የለሽ ሆኖአል፤ እናትና አባት የሌላቸውን ልጆች መብት አያስከብሩም፤ ለችግረኞችም ትክክለኛ ፍርድ አይፈርዱም።
“ካህናት ሆይ! ይህን ስሙ! እናንተም የእስራኤል ሕዝብ አስተውሉ! እናንተም ንጉሣውያን ቤተሰብ ይህን አድምጡ! እነሆ ፍርድ በእናንተ ላይ መጥቶአል፤ በምጽጳ እንደ ወጥመድ፥ በታቦርም እንደ ተዘረጋ መረብ ሆናችኋል።
ኢዮአታም፥ አካዝና ሕዝቅያስ በተከታታይ በይሁዳ በነገሡበት ዘመን እግዚአብሔር ለሞሬታዊው ለሚክያስ ስለ ሰማርያና ስለ ኢየሩሳሌም በራእይ በገለጠለት ጊዜ የተናገረው ቃል ይህ ነው፦
ከዚህም በኋላ እንዲህ አልኳቸው፦ “የእስራኤል ሕዝብ ልጆች መሪዎችና የእስራኤል ሕዝብ ገዢዎች! አድምጡ! ትክክለኛ ፍርድን ማወቅ ይገባችሁ አልነበረምን?
“ ‘መብት በመግፈፍ መጻተኞችን፥ ወላጆቻቸው የሞቱባቸው ልጆችንና ባሎቻቸው የሞቱባቸው መበለቶችን የሚያንገላታ ሁሉ የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይበሉ።