ሚክያስ 1:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ሚክያስ እንዲህ አለ፦ “በዚህ ምክንያት ‘ዋይ! ዋይ!’ እያልኩ አለቅሳለሁ፤ ሐዘኔንም ለመግለጥ ራቊቴንና ባዶ እግሬን እሄዳለሁ፤ እንደ ቀበሮ እጮኻለሁ፤ እንደ ሰጎንም የዋይታ ድምፅ አሰማለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ምክንያት አለቅሳለሁ፤ ዋይ ዋይም እላለሁ፤ ባዶ እግሬንና ዕርቃኔን እሄዳለሁ፤ እንደ ቀበሮ አላዝናለሁ፤ እንደ ጕጕትም አቃስታለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህ ምክንያት አለቅሳለሁ፥ ዋይ ዋይ እላለሁ፥ ባዶ እግሬንና ራቁቴን እሄዳለሁ፤ እንደ ቀበሮ አላዝናለሁ፥ እንደ ሰጎን ልጆችም የዋይታ ድምፅ አሰማለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ ነገር ዋይ ብላ ታለቅሳለች፥ ባዶ እግርዋንና ዕራቁትዋን ሆና ትሄዳለች፥ እንደ ቀበሮ ታለቅሳለች፥ እንደ ሰጐንም ዋይ ትላለች፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ ነገር ዋይ ብላ ታለቅሳለች፥ ባዶ እግርዋንና ዕራቁትዋን ሆና ትሄዳለች፥ እንደ ቀበሮ ታለቅሳለች፥ እንደ ሰጐንም ዋይ ትላለች፥ |
መርዶክዮስም ስለ ተደረገው ነገር ሁሉ በሰማ ጊዜ በሐዘን ልብሱን ቀደደ፤ ከዚህም በኋላ ማቅ ለብሶና በራሱ ላይ ዐመድ ነስንሶ ድምፁን ከፍ አድርጎ እየጮኸ በመረረ ሁኔታ በማልቀስ ወደ ከተማይቱ ውስጥ ገባ።
በታላላቅ ሕንጻዎችዋና በቤተ መንግሥትዋ ውስጥ የጅቦችና የተኲላዎች ጩኸት ያስተጋባል፤ እነሆ በዚህ ዐይነት ባቢሎን የምትጠፋበት ጊዜ ደርሶአል።”
ስለ ያዕዜር እንደማለቅስ ስለ ሲብማ የወይን ሐረጎችም አለቅሳለሁ፤ ስለ ሐሴቦንና ስለ ኤልዓሌ እንባዬ ይረግፋል፤ ሕዝቡ የሚደሰትበት መከር አልተገኘባቸውም፤
እስከ አሁን ከሐሳብና ከጭንቀት ነጻ ሆናችሁ በመቀማጠል ትኖሩ ነበር፤ አሁን ግን በፍርሃት ተንቀጥቀጡ! ልብሳችሁን አውልቃችሁ በወገባችሁ ላይ ማቅ ታጠቁ!
ወይ ሥቃይ! ይህን ሁሉ ሥቃይ እንዴት መታገሥ እችላለሁ! ወይ ልቤ! የልቤ አመታት እንዴት ፈጠነ? የጥሩምባ ድምፅና የጦርነት ድምፅ እየሰማሁ፥ ዝም ብዬ መታገሥ አልችልም።
እኔም እንዲህ አልኩ፦ “ሁሉም ወና ስለ ሆኑና በእነርሱም ላይ የሚዘዋወርባቸው ስለሌለ፥ ስለ ተራራዎች አዝናለሁ፤ ስለ ሜዳዎችም አለቅሳለሁ፤ የከብቶች ድምፅ ዳግመኛ አይሰማም፤ የሰማይ ወፎችና የምድር አራዊት ሁሉ ሸሽተው ጠፍተዋል።”
በጽዮን “ወዮልን ልንጠፋ ነው! ፈጽሞም ተዋረድን! ቤቶቻችን ስለ ፈራረሱ አገራችንን ለቀን መሄዳችን ነው” እየተባለ የሚያስተጋባውን የለቅሶ ጩኸት አድምጡ።
በዚያን ቀን ሰዎች ያፌዙባችኋል፤ እንዲህም እያሉ የምፀት ሙሾ ያወርዱላችኋል፦ “እኛ ፈጽሞ ጠፍተናል! እግዚአብሔር የሕዝባችንን ንብረት ወሰደብን፤ ርስታችንንም ለማራኪዎቻችን አከፋፈለ።”
ወደ ሳሙኤልም ፊት ሲቀርብ ልብሱን አውልቆ ትንቢት እየተናገረ፤ ቀኑንም ሌሊቱንም ሁሉ ራቁቱን በዚያው ተጋድሞ ዋለ፤ “ሳኦልም ከነቢያት እንደ አንዱ ሆኖ ተቈጠርን?” የሚለው የምሳሌ አነጋገር የመነጨው ከዚህ የተነሣ ነው።