ሚክያስ 2:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 በዚያን ቀን ሰዎች ያፌዙባችኋል፤ እንዲህም እያሉ የምፀት ሙሾ ያወርዱላችኋል፦ “እኛ ፈጽሞ ጠፍተናል! እግዚአብሔር የሕዝባችንን ንብረት ወሰደብን፤ ርስታችንንም ለማራኪዎቻችን አከፋፈለ።” Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም4 በዚያ ቀን ሰዎች ይሣለቁባችኋል፤ በሐዘን እንጕርጕሮ እንዲህ እያሉ ያፌዙባችኋል፤ ‘እኛ ፈጽሞ ጠፍተናል፤ የወገኔ ርስት ተከፋፍሏል። ከእኔ ነጥቆ ወስዶ፣ ዕርሻዎቻችንን ላሸነፉን አከፋፈለ።’ ” Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 በዚያ ቀን ምሳሌ ይመስልባችኋል፥ በኀዘን እንጉርጉሮ ያለቅስላችኋል፤ እርሱም፦ “ፈጽመን ጠፍተናል፤ የሕዝቤን ድርሻ ቀየረ፤ ከእኔ እንዴት ወሰደው፤ እርሻችንን ለከዳተኞች ይከፋፍላል” ይላል። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 በዚያ ቀን በምሳሌ ይመስሉባችኋል፥ በጽኑ ልቅሶም ያለቅሱላችኋል፥ እነርሱም፦ ፈጽመን ጠፍተናል፥ የሕዝቤን እድል ፈንታ ይሰፍራል፥ እርሱንም የሚከለክል የለም፥ እርሻችንን ለዓመፀኞች ይከፍላል ይላሉ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 በዚያ ቀን በምሳሌ ይመስሉባችኋል፥ በጽኑ ልቅሶም ያለቅሱላችኋል፥ እነርሱም፦ ፈጽመን ጠፍተናል፥ የሕዝቤን እድል ፈንታ ይሰፍራል፥ እርሱንም የሚከለክል የለም፥ እርሻችንን ለዓመፀኞች ይከፍላል ይላሉ። Ver Capítulo |