Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሚክያስ 1:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ምስሎችዋ ሁሉ ይሰባበራሉ፤ ለመቅደስዋ አመንዝሮች የተከፈለውም ሁሉ በእሳት ይቃጠላሉ፤ ጣዖቶችዋንም ሁሉ አጠፋለሁ፤ ሰማርያ እነዚህን ምስሎች የሰበሰበቻቸው የዝሙት ዋጋ መቀበያ ለማድረግ ነበር፤ አሁንም ጠላቶችዋ የዝሙት መጠቀሚያ ያደርጉአቸዋል።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ጣዖቶቿ ሁሉ ይሰባበራሉ፤ ለቤተ መቅደሷ የቀረበው ገጸ በረከት በእሳት ይቃጠላል፤ ምስሎቿን ሁሉ እደመስሳለሁ፤ ገጸ በረከቷን በዝሙት ዐዳሪነት እንደ ሰበሰበች ሁሉ፣ አሁንም ገጸ በረከቷ የዝሙት ዐዳሪነት ዋጋ መቀበያ ይሆናል።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 የተቀረጹትም ምስሎችዋ ይደቅቃሉ፥ በግልሙትና ያገኘችው ዋጋ ሁሉ በእሳት ይቃጠላል፥ ጣዖቶችዋንም ሁሉ አጠፋለሁ፤ በግልሙትና ዋጋ ሰብስባቸዋለችና፥ ወደ ግልሙትና ዋጋ ይመለሳሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 የተቀረጹትም ምስሎችዋ ይደቅቃሉ፥ በግልሙትና ያገኘችው ዋጋ ሁሉ በእሳት ይቃጠላል፥ ጣዖታትዋንም ሁሉ አጠፋለሁ፥ በግልሙትና ዋጋ ሰበሰባቻቸው፥ ወደ ግልሙትናም ዋጋ ይመለሳሉና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 የተቀረጹትም ምስሎችዋ ይደቅቃሉ፥ በግልሙትና ያገኘችው ዋጋ ሁሉ በእሳት ይቃጠላል፥ ጣዖታትዋንም ሁሉ አጠፋለሁ፥ በግልሙትና ዋጋ ሰበሰባቻቸው፥ ወደ ግልሙትናም ዋጋ ይመለሳሉና።

Ver Capítulo Copiar




ሚክያስ 1:7
22 Referencias Cruzadas  

ከበዓሉ ፍጻሜ በኋላ መላው የእስራኤል ሕዝብ ወደ ይሁዳ ከተሞች ሁሉ በመሄድ ከድንጋይ የተሠሩትን የጣዖት ዐምዶች ሰባበሩ፤ አሼራ ተብላ በምትጠራው ሴት አምላክ ስም የቆሙ ምስሎችንም ሰባብረው ጣሉ፤ መሠዊያዎችንና የአሕዛብ መስገጃ ስፍራዎችንም ደመሰሱ፤ እንዲሁም በቀሩት በይሁዳ፥ በብንያም፥ በኤፍሬምና በምናሴ ግዛቶች ውስጥ የነበሩትን የጣዖት መስገጃዎችንና መሠዊያዎችን ሁሉ አፈራረሱ፤ ከዚያም በኋላ ወደየመኖሪያ ስፍራዎቻቸው ተመለሱ።


ከሰባ ዓመት በኋላ እግዚአብሔር ጢሮስን ይጐበኛታል፤ ወደ ቀድሞ የንግድ ሥራዋ እንድትመለስ ያደርጋታል፤ በምድር ላይ ከሚገኙ መንግሥታት ሁሉ ጋር ታመነዝራለች።


እንግዲህ የያዕቆብ ልጆች እስራኤላውያን ለኃጢአታቸው ይቅርታ ማግኘት የሚችሉት የአሕዛብን የመሠዊያ ድንጋዮች እንደ ኖራ ፈጭተው፥ የዕጣን መሠዊያዎችንም ሆነ አሼራ ተብላ የምትጠራውን የሴት አምላክ ምስሎች ሲያስወግዱ ነው።


የምትኖሩባቸው ከተሞቻችሁ ሁሉ ባድማ ይሆናሉ፤ የመስገጃ ከፍተኛ ቦታዎቻችሁም ይፈርሳሉ፤ መሠዊያዎቻችሁ ፈርሰው ውድማ ይሆናሉ፤ ጣዖቶቻችሁ ተንኰታኲተው ይወድቃሉ፤ የዕጣን መሠዊያዎቻችሁም ይሰባበራሉ፤ የሠራችሁት ነገር ሁሉ እንዳልነበረ ይሆናል።


ከፍቅረኛዎችዋም ያገኘቻቸውን የወይን ተክሎችና የበለስ ዛፎች እነቃቅላለሁ፤ የወይንና የፍራፍሬ እርሻዎችዋን ወደ ጫካነት እለውጣለሁ፤ የዱር አራዊትም ይበሉአቸዋል።


ስለዚህ እንደገና ወደ በረሓ እወስዳታለሁ፤ እዚያም በፍቅር ቃል አባብዬ እማርካታለሁ።


እናታቸው አመንዝራ ስለ ሆነች እነርሱን ባሳፋሪ መንገድ ፀንሳቸዋለች፤ እርስዋም ይህን ያደረገችው ምግቤንና ውሃዬን፥ የሱፍና የተልባ እግር ልብሴን፥ ዘይቴንና መጠጤን የሚሰጡኝ ስለ ሆነ ፍቅረኞቼን ተከትዬ እሄዳለሁ ብላ ነው።


የሰማርያ ሕዝብ ሆይ! በጥጃ ምስል የተሠራ ጣዖታችሁን ተጸይፌአለሁ፤ ቊጣዬ በእናንተ ላይ እንደ እሳት ይነዳል፤ ከበደል የማትነጹት እስከ መቼ ነው?


ይህ በጥጃ ምስል የተሠራ ጣዖት በአናጢ እጅ የተሠራ ስለ ሆነ አምላክ ሊሆን አይችልም፤ ስለዚህ በጥጃ ምስል የተሠራው የሰማርያ ጣዖት ተሰባብሮ ይወድቃል።


የማረኩአቸውን ሕዝቤንም ለመከፋፈል ዕጣ ተጣጥለዋል፤ አመንዝራ ሴቶችን ለማግኘት ወንዶች ልጆችን ሰጡ፤ ወይን ጠጅ ለመጠጣትም ሴቶች ልጆችን ባሪያ አድርገው ሸጡ።


በየኰረብታው ላይ ያሉአችሁን መስገጃዎች እደመስሳለሁ፤ የዕጣን መሠዊያዎቻችሁንም አፈራርሳለሁ፤ ሬሳዎቻችሁንም በወደቁት ጣዖቶቻችሁ ላይ እጥላለሁ፤ ፈጽሞ እጸየፋችኋለሁ፤


እግዚአብሔር ዝሙትን ስለሚጠላ በዚህ ተግባር የተገኘ ገንዘብ የስእለትን መፈጸም የሚያመለክት ስጦታ ሆኖ ወደ እግዚአብሔር አምላክህ ቤት አይግባ።


ያንንም በጥጃ አምሳል አቅልጣችሁ የሠራችሁትን በኃጢአት የተሞላ አጸያፊ ምስል አንሥቼ እሳት ውስጥ ጣልኩት፤ እርሱንም ሰባብሬ እንደ ትቢያ አደቀቅሁት፤ ትቢያውንም ከተራራው በሚወርደው ውሃ ውስጥ ጨመርኩት።


የሚያሰክረውን የአመንዝራነትዋን ወይን ጠጅ ለሕዝቦች ሁሉ አጠጥታለች፤ የምድር ነገሥታት ከእርስዋ ጋር አመንዝረዋል፤ የምድር ነጋዴዎችም ከብዙ ምቾትዋ የተነሣ ሀብታሞች ሆነዋል።”


ከእርስዋ ጋር ያመነዘሩና በምቾት የኖሩ የምድር ነገሥታት እርስዋ ስትቃጠል የሚወጣውን ጢስ ሲያዩ ስለ እርስዋ እየጮኹ ያለቅሳሉ፤


በተከታዩም ቀን ማለዳ ተነሥተው ሲመለከቱ የምስሉ ሐውልት በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት እንደገና ወድቆ አዩት፤ በዚህ ጊዜ ራሱና ሁለት እጆቹ ተሰባብረው በመግቢያው መድረክ ላይ ወድቀው ሌላው አካሉ ብቻ ቀርቶ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos