Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሚክያስ 1:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 የሰማርያ ቊስል ሊፈወስ የሚችል አይደለም፤ ይህም ሥቃይ ወደ ይሁዳ ደርሶአል፤ ሕዝቤ ወደሚሰበሰቡበት ወደ ኢየሩሳሌም አደባባይም ተዛምቶአል።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ቍስሏ የማይሽር ነውና፤ ለይሁዳ ተርፏል፤ እስከ ሕዝቤ መግቢያ በር፣ እስከ ኢየሩሳሌም እንኳ ደርሷል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ቁስልዋ የማይፈወስ ነውና፤ ወደ ይሁዳ መጥቷል፥ ወደ ሕዝቤ በር ወደ ኢየሩሳሌምም ደርሶአል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ቁስልዋ የማይፈወስ ነውና፥ እስከ ይሁዳም ደርሶአልና፥ ወደ ሕዝቤም በር ወደ ኢየሩሳሌም ቀርቦአልና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ቁስልዋ የማይፈወስ ነውና፥ እስከ ይሁዳም ደርሶአልና፥ ወደ ሕዝቤም በር ወደ ኢየሩሳሌም ቀርቦአልና።

Ver Capítulo Copiar




ሚክያስ 1:9
15 Referencias Cruzadas  

የኢየሩሳሌም በሮች እርቃንዋን ሆና በልቅሶና በሐዘን እንደ ተቀመጠች ሴት ይሆናሉ።


ሕዝቅያስ በይሁዳ በነገሠ በዐሥራ አራተኛው ዓመት፥ የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም በተመሸጉት የይሁዳ ከተሞች ላይ አደጋ ጥሎ ያዛቸው።


ንጉሥ ሕዝቅያስ እጁን እንዲሰጥ ይጠይቀው ዘንድ የአሦር ንጉሥ የጦር አዛዡን፥ ከብዙ ሠራዊት ጋር ከላኪሽ ወደ ኢየሩሳሌም ላከው፤ እርሱም ሄዶ የላይኛው ኲሬ ውሃ በሚተላለፍበት ቦይ አካባቢ በሚገኘው በልብስ አጣቢው ቦታ አጠገብ ቆመ።


ሕመሜ የማይድነው፥ ቊስሌስ የማይጠገነውና የማይፈወሰው ለምንድን ነው? በበጋ ወራት እንደሚደርቅ ጅረት ተስፋ ታስቈርጠኛለህን?”


እንደ ድንግል የምትታዪ ግብጽ ሆይ! ወደ ገለዓድ ሄደሽ የሚቀባ መድኃኒት ፈልጊ፤ የአንቺ መድኃኒት ሁሉ ከንቱ ነው፤ ሊፈውስሽ የሚችል ነገር ከቶ የለም።


የማሮት ሕዝብ “መልካም ነገር ይመጣልናል” ብለው ተስፋ ያደርጋሉ። እግዚአብሔር ግን ጥፋትን በኢየሩሳሌም ላይ አውርዶአል።


ስለዚህ በኃጢአታችሁ ምክንያት እናንተን ለማጥፋትና ለመደምሰስ ተነሥቼአለሁ።


ክፉኛ የተጐዳሽ ስለ ሆነ ቊስልሽን ሊፈውስ የሚችል ነገር የለም፤ ማለቂያ ከሌለው ከአንቺ የጭካኔ ድርጊት ያመለጠ ሰው ስለሌለ ስለ አንቺ የሚሰሙ ሁሉ በአንቺ መውደቅ ያጨበጭባሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos