አንቺም እስከ ሰማይ ከፍ ያልሽው ቅፍርናሆም! ወደ ሲኦል ትወርጂአለሽ! በአንቺ የተደረጉት ተአምራት፥ በሰዶም ተደርገው ቢሆን ኖሮ ያቺ ከተማ ሳትጠፋ፥ እስከ ዛሬ በኖረች ነበር!
ማቴዎስ 4:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የናዝሬትንም ከተማ ትቶ፥ በዛብሎንና በንፍታሌም አውራጃ በገሊላ ባሕር አጠገብ ወደምትገኘው ወደ ቅፍርናሆም ከተማ መጥቶ ኖረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የናዝሬትንም ከተማ ትቶ፣ በዛብሎንና በንፍታሌም አካባቢ በባሕሩ አጠገብ በምትገኘው በቅፍርናሆም ከተማ ሄዶ መኖር ጀመረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ናዝሬትንም ትቶ በዛብሎንና በንፍታሌም ክልል ወደ አለችው በባሕር አጠገብ ወደምትገኝ ወደ ቅፍርናሆም መጥቶ ኖረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ናዝሬትንም ትቶ በዛብሎንና በንፍታሌም አገር በባሕር አጠገብ ወደ አለችው ወደ ቅፍርናሆም መጥቶ ኖረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ናዝሬትንም ትቶ በዛብሎንና በንፍታሌም አገር በባሕር አጠገብ ወደ አለችው ወደ ቅፍርናሆም መጥቶ ኖረ። |
አንቺም እስከ ሰማይ ከፍ ያልሽው ቅፍርናሆም! ወደ ሲኦል ትወርጂአለሽ! በአንቺ የተደረጉት ተአምራት፥ በሰዶም ተደርገው ቢሆን ኖሮ ያቺ ከተማ ሳትጠፋ፥ እስከ ዛሬ በኖረች ነበር!
ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ወደ ቅፍርናሆም በደረሱ ጊዜ የቤተ መቅደስ ግብር ተቀባዮች ወደ ጴጥሮስ ቀረቡና፥ “መምህራችሁ የቤተ መቅደስ ግብር አይከፍልምን?” ሲሉ ጠየቁት።
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “ ‘አንተ ሐኪም፥ እስቲ ራስህን አድን፥’ የሚለውን ምሳሌ እንደምትጠቅሱብኝ እርግጠኛ ነኝ፤ እንዲሁም ‘በቅፍርናሆም አድርገሃል ሲሉ የሰማነውን ሁሉ፥ እዚህም በገዛ አገርህ አድርግ’ ትሉኛላችሁ።
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ውሃውን የወይን ጠጅ ወደ ለወጠባት በገሊላ ምድር ወደምትገኘው ወደ ቃና ከተማ እንደገና ተመለሰ፤ በዚያን ጊዜ በቅፍርናሆም ልጁ የታመመበት አንድ የቤተ መንግሥት ሹም ነበረ።