Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዮሐንስ 6:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ሰዎቹም ኢየሱስ ወይም ደቀ መዛሙርቱ በእዚያ እንደሌሉ ባዩ ጊዜ በነዚያ ጀልባዎች ተሳፍረው ኢየሱስን ፍለጋ ወደ ቅፍርናሆም ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ሰዎቹም፣ ኢየሱስ ወይም ደቀ መዛሙርቱ በዚያ አለመኖራቸውን እንዳወቁ፣ ኢየሱስን ፍለጋ በጀልባዎቹ ወደ ቅፍርናሆም ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ሕዝቡም ኢየሱስ ወይም ደቀመዛሙርቱ በዚያ እንዳልነበሩ ባዩ ጊዜ፥ እራሳቸው በጀልባዎቹ ገብተው ኢየሱስን እየፈለጉ ወደ ቅፍርናሆም መጡ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 እነ​ዚያ ሰዎ​ችም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ፥ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም በዚያ እን​ዳ​ል​ነ​በሩ ባዩ ጊዜ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ይፈ​ል​ጉት ዘንድ በእ​ነ​ዚያ ታን​ኳ​ዎች ገብ​ተው ወደ ቅፍ​ር​ና​ሆም መጡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ሕዝቡም ኢየሱስ ወይም ደቀ መዛሙርቱ በዚያ እንዳልነበሩ ባዩ ጊዜ፥ ራሳቸው በጀልባዎቹ ገብተው ኢየሱስን እየፈለጉ ወደ ቅፍርናሆም መጡ።

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 6:24
11 Referencias Cruzadas  

በጀልባ ተሳፍረው ወደ ቅፍርናሆም አመሩ፤ በዚያን ሰዓት ጊዜው ጨልሞ ነበር፤ ኢየሱስም ገና ወደ እነርሱ አልመጣም ነበር።


ባገኙትም ጊዜ፥ “ሰዎች ሁሉ ይፈልጉሃል” አሉት።


ኢየሱስ፥ “አንቺ ሴት ስለ ምን ታለቅሺአለሽ፤ ማንንስ ትፈልጊአለሽ?” አላት። እርስዋም አትክልተኛው መስሎአት፥ “ጌታ ሆይ! አንተ ወስደኸው እንደ ሆነ የት እንዳኖርከው እባክህ ንገረኝ፤ እኔ እወስደዋለሁ” አለችው።


በበዓሉም ላይ “እርሱ የት ነው?” እያሉ አይሁድ ይፈልጉት ነበር።


ኢየሱስ ይህን የተናገረው በቅፍርናሆም በምኲራብ በሚያስተምርበት ጊዜ ነበር።


ሆኖም ሌሎች ጀልባዎች ከጥብርያዶስ ተነሥተው ኢየሱስ የምስጋና ጸሎት ወደአደረገበትና ሕዝቡ እንጀራ ወደ በላበት ስፍራ አጠገብ መጡ።


ሕዝቡ ይጠባበቀው ስለ ነበር ኢየሱስ ተመልሶ በመጣ ጊዜ ሁሉም በደስታ ተቀበሉት።


ባሕሩን ተሻግረው፥ ወደ ጌንሳሬጥ ደረሱ፤ ጀልባዋን ወደ ምድር አስጠግተው አሰሩ፤


ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ባሕሩን ተሻግረው ወደ ጌንሳሬጥ ምድር ደረሱ።


ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ እናንተ የምትፈልጉኝ እንጀራ ስለ በላችሁና ስለ ጠገባችሁ ነው እንጂ ተአምራት ስላያችሁ አይደለም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios