ስለዚህም ቤርሳቤህ የአዶንያስን ጉዳይ ልትነግር ወደ ንጉሡ ገባች፤ ንጉሡም ከተቀመጠበት ተነሥቶ እናቱን እጅ በመንሣት ተቀበላት፤ እርሱም በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠ በኋላ ሌላ ዙፋን አስመጥቶ በቀኙ አስቀመጣት፤
ማቴዎስ 20:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስም “ምን ትፈልጊያለሽ?” አላት። እርስዋም “በመንግሥትህ እነዚህ ሁለቱ ልጆቼ አንዱ በቀኝህ፥ አንዱ በግራህ እንዲቀመጡ አድርግልኝ!” አለችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም፣ “ምን ትፈልጊያለሽ?” አላት። እርሷም፣ “እነዚህ ሁለት ልጆቼ፣ በመንግሥትህ አንዱ በቀኝህ፣ አንዱ በግራህ እንዲቀመጡ ፍቀድ” አለችው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም “ምን ትፈልጊያለሽ?” አላት። እርሷም “እነዚህ ሁለቱ ልጆቼ በመንግሥትህ አንዱ በቀኝህ አንዱ በግራህ እንዲቀመጡ እዘዝ” አለችው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም “ምን ትፈልጊያለሽ?” አላት። እርስዋም “እነዚህ ሁለቱ ልጆቼ አንዱ በቀኝህ አንዱም በግራህ በመንግሥትህ እንዲቀመጡ እዘዝ፤” አለችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ ምን ትፈልጊያለሽ? አላት። እርስዋም፦ እነዚህ ሁለቱ ልጆቼ አንዱ በቀኝህ አንዱም በግራህ በመንግሥትህ እንዲቀመጡ እዘዝ አለችው። |
ስለዚህም ቤርሳቤህ የአዶንያስን ጉዳይ ልትነግር ወደ ንጉሡ ገባች፤ ንጉሡም ከተቀመጠበት ተነሥቶ እናቱን እጅ በመንሣት ተቀበላት፤ እርሱም በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠ በኋላ ሌላ ዙፋን አስመጥቶ በቀኙ አስቀመጣት፤
በቤተ መንግሥትህ ከሚገኙት ወይዛዝርት መካከል፥ የነገሥታት ሴቶች ልጆች ይገኛሉ፤ ንግሥቲቱም በንጹሕ ወርቅ ያሸበረቀ ጌጠኛ ልብስ ተጐናጽፋ ከዙፋንህ በስተቀኝ ቆማለች።
ታዲያ አንተ ለራስህ የተለየ መልካም ነገር እንዳደርግልህ ትፈልጋለህን? ይህን መፈለግ የለብህም፤ እኔ መቅሠፍትን በሰው ዘር ሁሉ ላይ አመጣለሁ፤ ይሁን እንጂ በምትሄድበት ቦታ ሁሉ ሌላው ቢቀር ሕይወትህ እንድትተርፍ አደርጋለሁ። እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “በእውነት እላችኋለሁ፤ የሰው ልጅ በክብር ዙፋን ላይ በሚቀመጥበት በአዲሱ ዓለም የእኔ ተከታዮች የሆናችሁ፥ እናንተም፥ በዐሥራ ሁለት ዙፋኑ ላይ ትቀመጣላችሁ፤ በዐሥራ ሁለቱም የእስራኤል ነገዶች ላይ ትፈርዳላችሁ።
ኢየሱስ ግን “እናንተ የምትለምኑትን አታውቁም፤ እኔ በቅርብ ጊዜ የምጠጣውን የመከራ ጽዋ መጠጣት ትችላላችሁን?” አላቸው። እነርሱም “አዎ እንችላለን!” አሉ።
ስለዚህም የሄሮዲያዳ ልጅ ወደ ግብዣው አዳራሽ ገብታ እየጨፈረች ሄሮድስንና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ተጋባዦች አስደሰተች፤ ንጉሡም ልጅትዋን፦ “የምትፈልጊውን ማንኛውንም ነገር ጠይቂኝ፤ እሰጥሻለሁ” አላት፤
ሰዎቹ ይህን በመስማት ላይ ሳሉ ኢየሱስ አንድ ምሳሌ ደግሞ ነገራቸው፤ እርሱ ወደ ኢየሩሳሌም ስለ ተቃረበ ሰዎቹ የእግዚአብሔር መንግሥት አሁኑኑ የምትገለጥ መስሎአቸው ነበር።
ማነው የሚፈርድ? ኢየሱስ ክርስቶስ ይፈርድባቸዋልን? እርሱ ስለ እኛ የሞተ፥ ከሞት ተነሥቶ በእግዚአብሔር አብ ቀኝ የተቀመጠ፥ ስለ እኛም የሚማልድ ነው።