ይህች ሴት የተቻላትን አድርጋለች፤ ሥጋዬም ከመቀበሩ በፊት አስቀድማ ለማዘጋጀት ሽቶ ቀባችው።
እርሷ ማድረግ የምትችለውን ያህል አድርጋለች፤ ለመቃብሬ እንዲሆን ሰውነቴን አስቀድማ ቀብታለች።
የተቻላትን አደረገች፤ አስቀድማ ለመቃብሬ ሥጋዬን ቀባችው።
መግዛት በምትጀምርበት ቀን ሕዝብህ ይገዙልሃል፤ የተቀደሰውን መጐናጸፊያ ደርበህ ከአጥቢያ ኮከብ በፊት እንደ ጠል ወለድኩህ።
እርስዋ ይህን ሽቶ በእኔ ላይ ማፍሰስዋ እኔን ለቀብር ለማዘጋጀት ነው።
ቀኑ መሽቶ ስለ ነበር የሰንበት ዋዜማና የዝግጅትም ጊዜ ሆነ፤
አስከሬኑንም አውርዶ በቀጭን ሐር ልብስ ከፈነው፤ ማንም ሰው ባልተቀበረበት ከአለት ተወቅሮ በተዘጋጀ መቃብር ውስጥ ቀበረው፤
ኢየሱስም እንዲህ አለ፦ “ለምቀበርበት ቀን ያደረገችው ዝግጅት ስለ ሆነ ተዉአት።
ለመስጠት መልካም ፈቃድ ካለ የሰው ልግሥና ተቀባይነት የሚያገኘው ባለው መጠን ሲሰጥ እንጂ በሌለው መጠን ሲሰጥ አይደለም።