ሉቃስ 23:49 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስን በቅርብ ያውቁት የነበሩ ሰዎች ሁሉና ከገሊላ ጀምሮ ይከተሉት የነበሩ ሴቶችም በሩቅ ቆመው ይህን ነገር ይመለከቱ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ኢየሱስን በቅርብ የሚያውቁት ሁሉ እንዲሁም ከገሊላ ጀምሮ የተከተሉት ሴቶች ይህን እየተመለከቱ ከሩቅ ቆመው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱን የሚያውቁት ሁሉ ግን ከገሊላ የተከተሉት ሴቶችም ጭምር በሩቅ ቆመው ይህን እያዩ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚያውቁት ሁሉና ከገሊላ ጀምሮ የተከተሉትም ሴቶች በሩቁ ቆመው ይህን ያዩ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚያውቁቱ ግን ሁሉ ከገሊላ የተከተሉት ሴቶችም ይህን እያዩ በሩቅ ቆመው ነበር። |
እንዲሁም ከርኩሳን መናፍስት የተላቀቁና ከበሽታ የተፈወሱ ሴቶች ኢየሱስን ይከተሉት ነበር፤ እነርሱም ሰባት አጋንንት የወጡላት መግደላዊት የተባለችው ማርያም፥