ሉቃስ 23:55 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም55 ኢየሱስን ተከትለው ከገሊላ የመጡ ሴቶች ከዮሴፍ ጋር ሄደው መቃብሩን አዩ፤ አስከሬኑም እንዴት እንደ ተቀበረ ተመለከቱ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም55 ከገሊላ ጀምሮ ከኢየሱስ ጋራ የመጡት ሴቶችም ተከትለው መቃብሩን አዩ፤ ሥጋውንም እንዴት እንዳስቀመጡት ተመለከቱ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)55 ከገሊላም ከእርሱ ጋር የመጡት ሴቶች ተከትለው መቃብሩን እንዲሁም አስከሬኑን እንዴት እንዳኖሩት አዩ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)55 ከገሊላም ከእርሱ ጋር የመጡ ሁለት ሴቶች ተከትለው፥ መቃብሩን፥ ሥጋውንም እንዴት እንዳኖሩት አዩ። ተመልሰውም ሽቱና ዘይት አዘጋጁ፤ ነገር ግን በሰንበት አልሄዱም፤ ሕጋቸው እንዲህ ነበርና። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)55 ከገሊላም ከእርሱ ጋር የመጡት ሴቶች ተከትለው መቃብሩን ሥጋውንም እንዴት እንዳኖሩት አዩ። Ver Capítulo |