ዘሌዋውያን 6:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማንም ሰው እነዚህን በደሎች ፈጽሞ ኃጢአተኛ ቢሆን፥ በቅሚያና በማታለል የወሰደውን፥ በዐደራ የተቀበለውንና ጠፍቶ ያገኘውን ንብረት ይመልስ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ሁኔታ ኀጢአት ቢሠራና በደለኛ ቢሆን፣ የሰረቀውን ወይም የቀማውን ወይም በዐደራ የተሰጠውን ወይም ጠፍቶ ያገኘውን ይመልሳል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ኃጢአትን ሠርቶ በደለኛ ቢሆን፥ በቅሚያ የወሰደውን ወይም በግፍ የተቀበለውን ወይም በአደራ ከእርሱ ዘንድ የተቀመጠውን ወይም ጠፍቶ ያገኘውን፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ ቢበድልና ከዚህ በኋላ ንስሓ ቢገባ፥ በቅድሚያ የወሰደውን፥ ወይም በዐመፅና በግፍ የተቀበለውን፥ ወይም የተሰጠውን አደራ፥ ወይም ጠፍቶ ያገኘውን፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ ኃጢአትን ሠርቶ በደለኛ ቢሆን፥ በቅሚያ የወሰደውን ወይም በግፍ የተቀበለውን ወይም የተሰጠውን አደራ ወይም ጠፍቶ ያገኘውን፥ |
ገንዘብም ሆነ እህል ወይም ወይንና የወይራ ዘይት ቢሆን ያበደራችሁትን ሁሉ ወለዱን ተዉላቸው፤ እርሻቸውን የወይንና የወይራ ዘይት ተክላቸውንና ቤታቸውን ሁሉ አሁኑኑ መልሱላቸው።”
የሸረሪት ድር ልብስ ለመሥራት አይጠቅምም፤ ማንም ለልብስ አይጠቀምበትም፤ ሥራቸው የበደል ሥራ ነው፤ እጆቻቸውም በዐመፅ ሥራ የተሞሉ ናቸው።
ድኾችንና ችግረኞችን ቢያስጨንቅ፥ ቢቀማ፥ ገንዘብ ሲያበድር በመያዣ ስም የወሰደውን ቢያስቀር፥ በአሕዛብ መስገጃ ስፍራዎች ጣዖትን ቢያመልክ አጸያፊ ነገሮችን ቢያደርግ፥
ይህም ማለት፥ ስለ ብድር በመያዣ ስም የያዘውን ወይም የሰረቀውን ንብረት ቢመልስ፥ ኃጢአት መሥራትን ትቶ ሕይወትን የሚሰጡ ሕጎችን ቢጠብቅ፥ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል እንጂ አይሞትም፤
ሕዝቡ ወደሚገኙበት ወደ ውጪው አደባባይ ከመውጣታቸው በፊት በቤተ መቅደስ ለአገልግሎት የተጠቀሙባቸውን አልባሳት አውልቀው በተቀደሱት ዕቃ ቤቶች ማኖርና ለራሳቸውም ሌላ ልብስ መልበስ አለባቸው፤ ይህንንም የሚያደርጉት ሕዝቡ ያልተፈቀደለትን የእነርሱን የተቀደሰ ልብስ ነክቶ እንዳይጐዳ ነው።
በዚያን ቀን በአሕዛብ የአምልኮ ሥርዓት በቤተ መቅደሱ መድረክ ላይ እየዘለሉ የሚያመልኩትንና የጌታቸውን ቤት በዓመፅና በማታለል በተገኙ ዕቃዎች የሚሞሉትን ሰዎች እቀጣለሁ።”
እነሆ፥ እናንተ እየተሳለቃችሁ ‘ይህ ሁሉ ምን አሰልቺ ነገር ነው!’ ትላላችሁ። የተሰረቀውን፥ አንካሳውን ወይም የታመመውን እንስሳ ለመሥዋዕትነት ታቀርባላችሁ፤ እኔ ይህን የምቀበል ይመስላችኋልን?