Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢዮብ 24:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 “ክፉ ሰዎች ድንበር ያፈርሳሉ። በጎችንም እየሰረቁ ያሰማራሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ሰዎች ድንበር ይገፋሉ፤ የሰረቁትን መንጋ ያሰማራሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 የድንበሩን ምልክት የሚያፈርሱ አሉ፥ መንጋዎቹን ቀምተው ያሰማራሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ኃጥ​ኣን የድ​ን​በ​ሩን ምል​ክት አለፉ፤ እረ​ኛ​ው​ንም ከመ​ን​ጋ​ዎቹ ጋር ይነ​ጥ​ቃሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 የድንበሩን ምልክት የሚያፈርሱ አሉ፥ መንጋዎቹን በዝብዘው ያሰማራሉ።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 24:2
10 Referencias Cruzadas  

የሳባ ሰዎች መጥተው አደጋ በመጣል ሁሉንም ዘርፈው ወሰዱ፤ አገልጋዮችህን ሁሉ በሰይፍ ገደሉአቸው፤ እኔ ብቻ አምልጬ የሆነውን ነገር ልነግርህ መጣሁ።”


ይኸኛው መልእክተኛ ተናግሮ ሳይጨርስ ሌላ መልእክተኛ መጥቶ፥ “በሦስት ቡድን የተከፈሉ የከለዳውያን ዘራፊዎች በድንገት አደጋ ጣሉብን፤ ግመሎቹን በሙሉ ወሰዱአቸው፤ አገልጋዮችህንም በሙሉ በሰይፍ ገደሉአቸው፤ እኔ ብቻ አምልጬ የሆነውን ነገር ልነግርህ መጣሁ” አለው።


ይህም የሚሆነው ድኻን ስለ ጨቈነና ያልሠራውንም ቤት በግፍ ስለ ወሰደ ነው።


“ሕጋዊ ባለርስቶችን ጨቊኜ ርስታቸውንም ነጥቄ አርሼ እንደ ሆነ


ሰብሉንም የተራቡ ሰዎች ይበሉታል፤ በእሾኽ መካከል የበቀለውን እንኳ አይተውለትም፤ የተጠሙ ሰዎችም ሀብቱን ለመውሰድ ይጐመዣሉ።


የቀድሞ አባቶችህ ያኖሩትን የወሰን ምልክት አትለውጥ።


የቈየውን የወሰን ምልክት አትለውጥ፤ እንዲሁም አባትና እናት የሌላቸውን ልጆች መሬት አትቀማ፤


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የይሁዳ መሪዎች የእስራኤልን ድንበር እንደሚያፈርሱ ሰዎች ሆነዋል፤ ስለዚህ እኔ ቊጣዬን እንደ ጐርፍ ውሃ አወርድባቸዋለሁ።


“እግዚአብሔር አምላክህ ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ለአንተ በተሰጠው ድርሻና በጐረቤትህ መካከል በቀድሞ ትውልድ የተተከለውን የድንበር ምልክት አታፍርስ።


“ ‘የጐረቤቱን ድንበር የሚያፈርስ ሁሉ የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይበሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos