ዘሌዋውያን 4:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሰፈር ውጪ ያውጣ፤ ዐመድ ወደሚፈስበት ርኩስ ወዳልሆነ ስፍራ በመውሰድ እንጨት ሰብስቦ ያንድድና በእሳት ያቃጥለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የወይፈኑን ብልት ሁሉ ከሰፈር ውጭ ዐመድ ወደሚፈስስበት በአምልኮው ሥርዐት መሠረት ንጹሕ ወደ ሆነው ስፍራ ይውሰደው፤ በተቈለለው ዐመድ ላይ ዕንጨት አንድዶ ያቃጥለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወይፈኑን ሁሉ ከሰፈሩ ውጭ አመድ ወደሚፈስበት ወደ ንጹሕ ስፍራ ይወስዳል፥ በእንጨትም ላይ በእሳት ያቃጥለዋል፤ አመድ በሚፈስስበት ስፍራ ይቃጠላል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወይፈኑን ሁሉ ከሰፈሩ ወደ ውጭ አመድ ወደሚፈስስበት ወደ ንጹሕ ስፍራ ይወስዱታል፤ በዕንጨትም ላይ በእሳት ያቃጥሉታል፤ አመድ በሚፈስስበት ስፍራ ይቃጠላል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈርሱንም፥ ወይፈኑን ሁሉ ከሰፈሩ ወደ ውጭ አመድ ወደሚፈስስበት ወደ ንጹሕ ስፍራ ይወስደዋል፥ በእንጨትም ላይ በእሳት ያቃጥለዋል፤ አመድ በሚፈስስበት ስፍራ ይቃጠላል። |
ለኃጢአት ስርየት መሥዋዕት ሆኖ የቀረበውንም ኰርማ ወስደህ ለቤተ መቅደሱ ከተከለለው የተቀደሰ ቦታ ውጪ ለዚህ በተወሰነው ስፍራ ታቃጥለዋለህ።
ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት ሆነው የቀረቡትና ኃጢአትን ለማስተስረይ ደማቸው ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ገብቶ የነበረው ኰርማና ፍየልም ከሰፈር ወደ ውጪ ተወስደው በእሳት ይቃጠሉ፤ እንዲሁም ቆዳቸው፥ ሥጋቸውና የሆድ ዕቃቸው በሙሉ ይቃጠል።
ከዚህም በኋላ ኰርማውን ከሰፈር ወደ ውጪ አውጥቶ ስለ ራሱ በደል በቀረበው ወይፈን ላይ እንደተፈጸመው ዐይነት ያቃጥለው፤ ይህም የማኅበረሰቡን ኃጢአት የሚያስወግድ መሥዋዕት ይሆናል።
ማንም ሰው እነዚህን በደሎች ፈጽሞ ኃጢአተኛ ቢሆን፥ በቅሚያና በማታለል የወሰደውን፥ በዐደራ የተቀበለውንና ጠፍቶ ያገኘውን ንብረት ይመልስ፤
በመካከላቸው እኔ የምኖርበትን ሰፈራቸውን እንዳያረክሱ፥ እነዚህን ያልነጹ ሰዎች ሁሉ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች ከመካከላችሁ ወጥተው እንዲባረሩ አድርጉ።”
የአይሁድ የካህናት አለቃ የኃጢአት ይቅርታን የሚያስገኘውን የእንስሳት ደም ይዞ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ይገባል፤ የእንስሳቱ በድን ግን ከሰፈሩ ውጪ ይቃጠላል፤