አሮንም በግንባሩ ላይ ያድርገው፤ በዚህ ዐይነት ባቀራረብ እንኳ ስሕተት ቢፈጽሙ እስራኤላውያን የሚያቀርቡልኝን መባ ሁሉ እኔ እግዚአብሔር እቀበላቸዋለሁ።
ዘሌዋውያን 23:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ይቀበላችሁ ዘንድ ካህኑ ነዶውን በመወዝወዝ ለእግዚአብሔር ልዩ መባ አድርጎ ያቀርባል። ካህኑም እርሱን ማቅረብ ያለበት ከሰንበት ቀጥሎ በሚውለው ቀን ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነዶው ተቀባይነት እንዲያገኝላችሁም በእግዚአብሔር ፊት ይወዝውዘው፤ ካህኑ ነዶውን የሚወዘውዘው በሰንበት ቀን ማግስት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ነዶውን በጌታ ፊት እንዲሠምርላችሁ ይወዝውዘው፤ ካህኑ የሚወዘውዘው በማግስቱ ከሰንበት በኋላ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም ነዶውን በእግዚአብሔር ፊት እንዲሠምርላችሁ ያቀርበዋል፤ በማግስቱ ከሰንበት በኋላ ካህኑ ያቅርበው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም ነዶውን በእግዚአብሔር ፊት እንዲሠምርላችሁ ይወዝውዘው፤ በማግስቱ ከሰንበት በኋላ ካህኑ ይወዝውዘው። |
አሮንም በግንባሩ ላይ ያድርገው፤ በዚህ ዐይነት ባቀራረብ እንኳ ስሕተት ቢፈጽሙ እስራኤላውያን የሚያቀርቡልኝን መባ ሁሉ እኔ እግዚአብሔር እቀበላቸዋለሁ።
ነገር ግን በመወዝወዝ ልዩ መባ ሆኖ ለእግዚአብሔር ከቀረበ በኋላ የካህናቱ ድርሻ እንዲሆን ስለ ተፈቀደ ፍርምባውንና ወርቹን አንተና ቤተሰብህ ሴቶች ልጆችህ ጭምር ትበሉታላችሁ፤ ይህንንም በተቀደሰ ስፍራ ትበሉታላችሁ፤ ይህም የእስራኤል ሕዝብ የአንድነት መሥዋዕት አድርገው ከሚያቀርቡት መባ ሁሉ ተከፍሎ ለአንተና ለልጆችህ ተሰጥቶአል።
“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ እኔ እግዚአብሔር ወደምሰጣችሁ ምድር ገብታችሁ መከር በምታጭዱበት ጊዜ የመጀመሪያውን ነዶ ለካህኑ ስጡ፤
የእህል መባችሁን በምታቀርቡበት በዚያኑ ቀን ነውር የሌለበትና አንድ ዓመት የሆነውን የበግ ጠቦት የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጋችሁ አብራችሁ አቅርቡ።
እንግዲህ ናዖሚ ከሞአባዊት ምራትዋ ከሩት ጋር ከሞአብ አገር የተመለሰችው በዚህ ሁኔታ ነበር፤ እነርሱ ቤተልሔም በደረሱ ጊዜ የገብስ መከር የሚሰበሰብበት ወቅት መጀመሩ ነበር።