Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘሌዋውያን 23:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 የእህል መባችሁን በምታቀርቡበት በዚያኑ ቀን ነውር የሌለበትና አንድ ዓመት የሆነውን የበግ ጠቦት የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጋችሁ አብራችሁ አቅርቡ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ነዶውን በምትወዘውዙበት ቀን እንከን የሌለበትን የአንድ ዓመት ተባዕት የበግ ጠቦት የሚቃጠል መሥዋዕት እንዲሆን ለእግዚአብሔር አቅርቡ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ነዶውንም በወዘወዛችሁበት ቀን ነውር የሌለበትን የአንድ ዓመት ተባት ጠቦት ለሚቃጠል መሥዋዕት ለጌታ አቅርቡ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ነዶ​ው​ንም ባቀ​ረ​ባ​ች​ሁ​በት ቀን ነውር የሌ​ለ​በ​ትን የአ​ንድ ዓመት ተባት ጠቦት ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቅ​ርቡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ነዶውንም በወዘወዛችሁበት ቀን ነውር የሌለበትን የአንድ ዓመት ተባት ጠቦት ለሚቃጠል መሥዋዕት ወደ እግዚአብሔር አቅርቡ።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 23:12
7 Referencias Cruzadas  

የምትመርጡት እንስሳ በግ ወይም ፍየል መሆን ይችላል፤ ነገር ግን ምንም ነውር የሌለበትና አንድ ዓመት የሞላው ተባዕት ይሁን።


ሰውየው ከበግ ወይም ከፍየል መንጋዎቹ አንዱን ለሚቃጠል መሥዋዕት ማቅረብ ቢፈልግ ምንም ነውር የሌለበት ተባዕት ይሁን።


ይኸውም ከቀንድ ከብቱ መካከል አንዱን ለሚቃጠል መሥዋዕት ማቅረብ ቢፈልግ ምንም ነውር የሌለበትን ኰርማ መርጦ ያምጣ፤ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት የሰመረ መሥዋዕት ይሆንለት ዘንድ በመገናኛው ድንኳን መግቢያ በር በኩል ያቅርበው።


እግዚአብሔር ይቀበላችሁ ዘንድ ካህኑ ነዶውን በመወዝወዝ ለእግዚአብሔር ልዩ መባ አድርጎ ያቀርባል። ካህኑም እርሱን ማቅረብ ያለበት ከሰንበት ቀጥሎ በሚውለው ቀን ነው።


ከእርሱም ጋር በወይራ ዘይት የተለወሰ ሁለት ኪሎ የላመ ዱቄት የምግብ መሥዋዕት አድርጋችሁ አቅርቡ፤ ይህም መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ የሚቃጠል መሥዋዕት ይሆናል፤ ከዚህም ጋር አንድ ሊትር የሚሆን የወይን ጠጅ ስጦታ ታቀርባላችሁ።


እናንተ የተዋጃችሁት ነውር ወይም እንከን እንደሌለው ንጹሕ በግ በሆነው በክርስቶስ ክቡር ደም ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos