Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘሌዋውያን 23:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 እር​ሱም ነዶ​ውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እን​ዲ​ሠ​ም​ር​ላ​ችሁ ያቀ​ር​በ​ዋል፤ በማ​ግ​ስቱ ከሰ​ን​በት በኋላ ካህኑ ያቅ​ር​በው፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ነዶው ተቀባይነት እንዲያገኝላችሁም በእግዚአብሔር ፊት ይወዝውዘው፤ ካህኑ ነዶውን የሚወዘውዘው በሰንበት ቀን ማግስት ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 እርሱም ነዶውን በጌታ ፊት እንዲሠምርላችሁ ይወዝውዘው፤ ካህኑ የሚወዘውዘው በማግስቱ ከሰንበት በኋላ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እግዚአብሔር ይቀበላችሁ ዘንድ ካህኑ ነዶውን በመወዝወዝ ለእግዚአብሔር ልዩ መባ አድርጎ ያቀርባል። ካህኑም እርሱን ማቅረብ ያለበት ከሰንበት ቀጥሎ በሚውለው ቀን ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እርሱም ነዶውን በእግዚአብሔር ፊት እንዲሠምርላችሁ ይወዝውዘው፤ በማግስቱ ከሰንበት በኋላ ካህኑ ይወዝውዘው።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 23:11
7 Referencias Cruzadas  

በአ​ሮ​ንም ግን​ባር ላይ ይሆ​ናል፤ አሮ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በሚ​ያ​ቀ​ር​ቡ​ትና በሚ​ቀ​ድ​ሱት በቅ​ዱሱ ስጦ​ታ​ቸው ሁሉ ላይ የሠ​ሩ​ትን ኀጢ​አት ይሸ​ከም፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ተቀ​ባ​ይ​ነት ያለው እን​ዲ​ሆ​ን​ላ​ቸው ሁል​ጊዜ በግ​ን​ባሩ ላይ ይሁን።


ሁሉ​ንም በአ​ሮን እጆ​ችና በል​ጆቹ እጆች ታኖ​ረ​ዋ​ለህ፤ ለሚ​ለይ ቍር​ባን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ትለ​የ​ዋ​ለህ።


እነ​ዚ​ህም ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ቶች ለአ​ን​ተና ለል​ጆ​ችህ ሥር​ዐት እን​ዲ​ሆኑ ስለ ተሰጡ፥ የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቱን ፍር​ም​ባና ወርች አንተ፥ ከአ​ንተ ጋርም ልጆ​ችህ፥ ቤተ​ሰ​ብ​ህም ተለ​ይቶ በን​ጹሕ ስፍራ ትበ​ላ​ላ​ችሁ።


“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ ወደ​ም​ሰ​ጣ​ችሁ ምድር በገ​ባ​ችሁ ጊዜ፥ መከ​ሩ​ንም ባጨ​ዳ​ችሁ ጊዜ፥ የእ​ና​ን​ተን መከር በኵ​ራት ነዶ ወደ ካህኑ አምጡ፤


ነዶ​ው​ንም ባቀ​ረ​ባ​ች​ሁ​በት ቀን ነውር የሌ​ለ​በ​ትን የአ​ንድ ዓመት ተባት ጠቦት ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቅ​ርቡ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው አሮን ፍር​ም​ባ​ዎ​ቹ​ንና ቀኝ ወር​ቹን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለየ።


ኑኃሚንም ከእርስዋም ጋር ከሞዓብ ምድር የተመለሰችው ሞዓባዊቱ ምራትዋ ሩት ተመለሱ። የገብስም መከር በተጀመረ ጊዜ ወደ ቤተልሔም መጡ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos