ዘሌዋውያን 21:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሊቀ ካህናቱ የቅባት ዘይት በራሱ ላይ የፈሰሰበትና የክህነትንም ልብስ ይለብስ ዘንድ የተቀደሰ ስለ ሆነ፥ ሰው በሞተ ጊዜ ሐዘኑን ለመግለጥ ጠጒሩን አይላጭ፤ ልብሱንም አይቅደድ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ከወንድሞቹ መካከል ተለይቶ በራሱ ላይ ዘይት የፈሰሰበትና የክህነት ልብስ እንዲለብስ የተቀባው ካህን የራስ ጠጕሩን አይንጭ፤ ወይም ልብሱን አይቅደድ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በራሱም ላይ የቅባዓት ዘይት የፈሰሰበት፥ የክህነትም ልብስ እንዲለብስ የተቀደሰው፥ ከወንድሞቹ ይበልጥ ከፍ ያለው ካህን የራሱን ጠጉር አያጐስቁል ልብሱንም አይቅደድ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በራሱም ላይ የቅባት ዘይት የፈሰሰበት፥ የክህነትም ልብስ ይለብስ ዘንድ የተቀደሰ፥ ከወንድሞቹ የተለየው ካህን ራሱን አይላጭ፤ ልብሱንም አይቅደድ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በራሱም ላይ የቅባት ዘይት የፈሰሰበት፥ የክህነትም ልብስ ይለብስ ዘንድ የተቀደሰ ከወንድሞቹ የበለጠው ካህን ራሱን አይግለጥ ልብሱንም አይቅደድ። |
ዳዊትም ሐዘኑን በመግለጥ ጫማ ሳያደርግ ራሱን ተከናንቦ የደብረ ዘይትን አቀበት እያለቀሰ ወጣ፤ የተከተሉትም ሁሉ ደግሞ ራሳቸውን ተከናንበው ያለቅሱ ነበር።
ከዚህ በኋላ መርዶክዮስ ወደ ቤተ መንግሥቱ መግቢያ ተመልሶ ሲሄድ፥ ሃማን ከኀፍረቱ ብዛት የተነሣ ራሱን በመከናነብ ወደ መኖሪያ ቤቱ ፈጥኖ ሄደ።
በሐዘንም መንሰቅሰቅህን ሰው አይስማህ፤ ለሟችዋ አታልቅስ፤ መጠምጠሚያህንም በራስህ ላይ አድርግ፤ ጫማህንም በእግርህ አጥልቅ፤ አፍህን አትሸፍን፤ የእዝን እንጀራ አትብላ።”
“በዚህ ዐይነት የሥጋ ደዌ በሽታ ያለበት ሰው የተቀዳደደ ልብስ ይልበስ፤ ጠጒሩን አያበጥር፥ ከንፈሩን ይሸፍን፤ ከዚያም በኋላ ‘እኔ የረከስኩ ነኝ! የረከስኩ ነኝ!’ እያለ ይጩኽ።
“ተቀብቶ የተሾመው ካህን ኃጢአት ሠርቶ ሕዝቡን እንደ በደለኛ የሚያስቈጥር ሆኖ ቢገኝ፥ ምንም ነውር የሌለበትን አንድ ወይፈን ያምጣ፤ ስለ ኃጢአቱም ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርጎ ያቅርበው።
ማኅበሩ በግድያ ወንጀል የተከሰሰውን ሰው ከተበቃይ እጅ በመታደግ አምልጦ ወደነበረበት ወደ መማጠኛ ከተማዋ መመለስ አለበት፤ በዘመኑ ሊቀ ካህናት የሆነው ሰው እስከሚሞትበት ድረስ እዚያው መቈየት ይኖርበታል።
ለአምላኩ ያቀረበው የናዝራዊነት ስእለት በራሱ ላይ ስለ ሆነ አባቱ ወይም እናቱ፥ ወንድሙ ወይም እኅቱ ቢሞቱ አስከሬናቸውን በመንካት ራሱን አያርክስ።
በዚህ ጊዜ የካህናት አለቃው በብስጭት ልብሱን ቀደደና እንዲህ አለ፤ “እነሆ፥ በእግዚአብሔር ላይ የስድብ ቃል ተናግሮአል! እናንተም ስድቡን ሰምታችኋል! ከዚህ የበለጠ ምን ምስክር ያስፈልጋል!