ሰቈቃወ 5:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀንበር እንደተጫኑ እንስሶች በመነዳት እጅግ ደክመናል፤ እንድናርፍም አይፈቀድልንም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚያሳድዱን ከተረከዞቻችን ሥር ናቸው፤ ተጨንቀናል ዕረፍትም ዐጥተናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሳዳጆቻችን በአንገታችን ላይ ናቸው፥ እኛ ደክመናል ዕረፍትም የለንም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጠላቶቻችን አሳደዱን፤ እኛም ደክመናል፤ ዕረፍትም የለንም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሳዳጆቻችን በአንገታችን ላይ ናቸው፥ እኛ ደክመናል ዕረፍትም የለንም። |
“ነገር ግን ማንኛውም ሕዝብ ወይም መንግሥት ‘እርሱን አላገለግልም፤ በቀንበሩም ሥር ሆኜ አልገዛም’ ቢል ናቡከደነፆር ራሱ እንዲደመስሰው እስከ ፈቀድኩለት ድረስ፥ በጦርነት፥ በራብና በወረርሽኝ እንዲቀጡ አደርጋለሁ።
በእነዚህ ሕዝቦች ሁሉ ጫንቃ ላይ የብረት ቀንበር እጭናለሁ፤ እነርሱም ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር ይገዙለታል፤ ሌላው ቀርቶ የምድረ በዳ እንስሶች ሁሉ እንዲገዙለት አደርጋለሁ፤’ እኔ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ይህን ተናግሬአለሁ።”
ሰፊው የባቢሎን ቅጽር ወድቆ ከመሬት ይደባለቃል፤ ከፍ ብለው የተሠሩ የቅጽር በሮችዋ በእሳት ይጋያሉ። የሕዝብዋ ድካም ከንቱ ይሆናል፤ ሕዝቦች የደከሙበት ነገር ሁሉ በእሳት ይወድማል። እኔ የሠራዊት አምላክ ይህን ተናግሬአለሁ።”
የይሁዳ ሕዝብ ከጭንቀትና ከከባድ የባርነት ሥራ በኋላ ወደ ምርኮ ተወሰዱ፤ አሁን እነርሱ በሕዝቦች መካከል ሲኖሩ ዕረፍት አያገኙም፤ እነርሱ በጭንቀት ውስጥ እያሉ አሳዳጆቻቸው ደረሱባቸው።
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እነሆ በእናንተ ላይ ጥፋትን አመጣለሁ፤ ከዚህም ልታመልጡ ፈጽሞ አትችሉም፤ ያ አሠቃቂ ጊዜ ስለሚሆን በትዕቢት መመላለስ አትችሉም።
ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ እግዚአብሔር በአንተ ላይ ለሚልካቸው ለጠላቶችህ አገልጋይ ትሆናለህ። በሁሉ ነገር በመቸገርም ትራባለህ፤ ትጠማለህ፤ ትታረዛለህ። ፈጽሞ እስክትጠፋ ድረስ እግዚአብሔር አንተን በጠላቶችህ እንደ ብረት በጠነከረ የአገዛዝ ቀንበር በብርቱ እንድትጨቈን ያደርጋል።