እኔን ከጒዳት ሁሉ ያዳነኝ መልአክ እነርሱንም ይጠብቃቸው። የእኔ ስም፥ የአባቶቼም የአብርሃምና የይስሐቅ ስም በነዚህ ልጆች ሲታወስ ይኑር፤ ዘራቸውም በምድር ላይ ይብዛ።”
ሰቈቃወ 3:58 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ጌታ ሆይ! የእኔን ጉዳይ ተከታትለህ ሕይወቴን አዳንክ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታ ሆይ፤ ለእኔ ተሟገትኽልኝ፤ ሕይወቴንም ተቤዠህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሬስ። ጌታ ሆይ፥ ስለ ነፍሴ ተምዋግተህ ሕይወቴን ተቤዠህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሬስ። አቤቱ፥ የነፍሴን ፍርድ ፈረድህ፤ ሕይወቴንም ተቤዥህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሬስ። ጌታ ሆይ፥ ስለ ነፍሴ ተምዋግተህ ሕይወቴን ተቤዠህ። |
እኔን ከጒዳት ሁሉ ያዳነኝ መልአክ እነርሱንም ይጠብቃቸው። የእኔ ስም፥ የአባቶቼም የአብርሃምና የይስሐቅ ስም በነዚህ ልጆች ሲታወስ ይኑር፤ ዘራቸውም በምድር ላይ ይብዛ።”
የሕዝቡን አቤቱታ የሚመለከተው አምላካችሁ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እንደ ሰከረ ሰው የሚያንገዳግደውን የመከራ ጽዋ ከእጃችሁ ወስጄአለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲያ ኀይለኛ ቊጣዬን ከትልቁ ዋንጫ አትጠጡም።
እኔም እንዲህ በማለት ጸለይኩ፦ “የሠራዊት አምላክ ሆይ! የሰውን ልብና አእምሮ የምትመረምር አንተ ቅን ፈራጅ ነህ፤ እነሆ ችግሬን ለአንተ አስታወቅሁ፤ ስለዚህም በእነዚህ ሕዝብ ላይ የምትፈጽመውን በቀል እንዳይ አድርገኝ።”
ነገር ግን ታዳጊያቸው ብርቱ ነው፤ ስሙም የሠራዊት አምላክ ነው፤ እርሱ ራሱ ይረዳቸዋል፤ ሰላምን በምድር ላይ ያወርድላቸዋል፤ በባቢሎን ሕዝብ ላይ ገና መከራን ያመጣባቸዋል።”
ስለዚህ እግዚአብሔር ለኢየሩሳሌም ሕዝብ እንዲህ ይላል፦ “እኔ እናንተን እረዳለሁ፤ ባቢሎናውያንንም እበቀልላችኋለሁ፤ የባቢሎን የውሃ ምንጭና ወንዞችዋ ሁሉ እንዲደርቁ አደርጋለሁ።
ዳዊትም የናባልን መሞት በሰማ ጊዜ “እኔን በመስደቡ እግዚአብሔር ናባልን ስለ ተበቀለውና እኔንም ከስሕተት ስለ ጠበቀኝ እግዚአብሔር ይመስገን፤ እርሱ ናባልን ስለ ክፉ ሥራው ቀጥቶታል” አለ። ከዚህም በኋላ ዳዊት ወደ አቢጌል መልእክተኛ ልኮ ሊያገባት መፈለጉን ገለጠላት።