Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 103:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ወደ መቃብር ከመውረድ ይጠብቀኛል፤ በፍቅርና በምሕረትም ይባርከኛል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ሕይወትሽን ከጥፋት ጕድጓድ የሚያድን፣ ምሕረትንና ርኅራኄን የሚያቀዳጅሽ፣

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ሕይወትሽን ከጥፋት የሚያድናት፥ በፍቅርና በርኅራኄ የሚከልልሽ፥

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 መላ​እ​ክ​ቱን መን​ፈስ፥ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹ​ንም የእ​ሳት ነበ​ል​ባል የሚ​ያ​ደ​ር​ጋ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 103:4
15 Referencias Cruzadas  

ያዳንከኝ እኔ የምስጋና መዝሙር ስዘምርልህ። ከንፈሮቼ የደስታ ጩኸት ይጮኻሉ።


አንተ ከሞት አድነኸኛል፤ ተሰናክዬ እንዳልወድቅም ረድተኸኛል፤ ስለዚህ በሕያዋን ላይ በሚያበራው ብርሃን በእግዚአብሔር ፊት እመላለሳለሁ።


ምሥራቅ ከምዕራብ የሚርቀውን ያኽል እግዚአብሔር ኃጢአታችንን ከእኛ ያርቀዋል።


ይህን ብታደርጉ ዋናው እረኛ በሚገለጥበት ጊዜ የማይበላሸውን የክብር አክሊል ትቀበላላችሁ።


ከመላእክት በጥቂቱ ብታሳንሰውም፥ የክብርና የምስጋና ዘውድ ጫንክለት፤


እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ጻድቃንን ትባርካለህ፤ በቸርነትህም እንደ ጋሻ መከላከያ ትሆንላቸዋለህ።


ጌታ በቃል ኪዳኑ መሠረት ለወዳጆቹ የሚሰጠውን የሕይወት አክሊል ስለሚቀበል ፈተናን ታግሦ የሚጸና ሰው የተባረከ ነው።


እግዚአብሔር የአገልጋዮቹን ሕይወት ያድናል፤ በእርሱ የተማጠኑትም ክፉ ነገር አይደርስባቸውም።


አዲስ መዝሙርም እንዲህ እያሉ ዘመሩ፦ “በደምህ ከየነገዱ፥ ከየቋንቋው፥ ከየወገኑ፥ ከየሕዝቡ ሰዎችን ለእግዚአብሔር ለመዋጀት፥ አንተ ስለ ታረድህ የብራናውን ጥቅል መጽሐፍ ለመውሰድና ማኅተሞቹን ለመክፈት የተገባህ ሆነሃል፤


በብዙ በረከትን ሰጥተህ ተቀበልከው፤ በራሱ ላይ የንጹሕ ወርቅ ዘውድ ደፋህለት።


እኔን ከጒዳት ሁሉ ያዳነኝ መልአክ እነርሱንም ይጠብቃቸው። የእኔ ስም፥ የአባቶቼም የአብርሃምና የይስሐቅ ስም በነዚህ ልጆች ሲታወስ ይኑር፤ ዘራቸውም በምድር ላይ ይብዛ።”


በአንተ ቸርነት የሚገኘው መከር እንዴት ብዙ ነው! አንተ በምትገኝበት ቦታ ሁሉ ብዙ ሰብል አለ።


ችግር የደረሰብኝ በእርግጥ ለደኅንነቴ ነው፤ ከአደጋም ሁሉ ሕይወቴን ታድናለህ፤ ኃጢአቴንም ሁሉ ይቅር ትላለህ።


እጅግ ከመቈጣቴ የተነሣ ለጥቂት ጊዜ ትቼሽ ነበር፤ ነገር ግን በዘለዓለማዊ ፍቅሬ እራራልሻለሁ፤ ይላል አዳኝሽ እግዚአብሔር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios