እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ “በእርግጥ በወንድማችን ላይ ስላደረስነው በደል ተገቢውን ቅጣት በመቀበል ላይ ነን፤ ምሕረት እንድናደርግለት ተጨንቆ ሲለምነን ልመናውን አልተቀበልንም ነበር፤ በእኛም ላይ ይህ ጭንቀት ሊደርስብን የቻለው በዚህ ምክንያት ነው።”
ኢያሱ 7:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዓካንም እንዲህ ሲል መለሰ፥ “እውነት ነው፤ የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን የበደልኩ እኔ ነኝ፤ እነሆ፥ ያደረግኹትም ከዚህ የሚከተለው ነው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አካንም መልሶ ኢያሱን እንዲህ አለው፤ “እውነት ነው! የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን በድያለሁ፤ ያደረግሁትም ይህ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አካንም መልሶ ኢያሱን እንዲህ አለው፦ “በእውነት በእስራኤል አምላክ በጌታ ላይ ኃጢአት ሠርቻለሁ እንዲህና እንዲህም አድርጌአለሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አካንም መልሶ ኢያሱን፥ “በእውነት በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ፊት በድያለሁ፤ እንዲህና እንዲህም አድርጌአለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አካንም መልሶ ኢያሱን፦ በእውነት የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን በድያለሁ እንዲህና እንዲህም አድርጌአለሁ። |
እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ “በእርግጥ በወንድማችን ላይ ስላደረስነው በደል ተገቢውን ቅጣት በመቀበል ላይ ነን፤ ምሕረት እንድናደርግለት ተጨንቆ ሲለምነን ልመናውን አልተቀበልንም ነበር፤ በእኛም ላይ ይህ ጭንቀት ሊደርስብን የቻለው በዚህ ምክንያት ነው።”
እርሱም በሰዎች ፊት እንዲህ ብሎ ይዘምራል፤ ‘እኔ ኃጢአት ሠርቻለሁ፤ የቀናውንም ነገር አጣምሜአለሁ፤ እግዚአብሔር ግን በደሌን አልቈጠረብኝም።
አንተ ሰዎችን በመቈጣጠር የምትከታተል አምላክ ሆይ፥ እኔ ኃጢአት በመሥራቴ አንተ ምን ተበደልክ? ስለምን ዒላማ አደረግኸኝ? ይህን ያኽል ከባድ ሸክም ሆንኩብህን?
በለዓምም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “በእርግጥ ኃጢአት ሠርቻለሁ፤ አንተ እኔን ለመቃወም በመንገድ ላይ መቆምህን አላወቅሁም ነበር፤ አሁንም ወደዚያ መሄዴ ስሕተት መስሎ ከታየህ ወደ ቤቴ እመለሳለሁ።”
ካገኘነው ዕቃ መካከል ውብ የሆነ የባቢሎናውያን ካባ፥ ሁለት ኪሎ ያኽል የሚመዝን ብርና ግማሽ ኪሎ ያህል የሚመዝን ምዝምዝ ወርቅ አየሁ፤ እነርሱንም ለማግኘት ብርቱ ፍላጎት ስላደረብኝ ወስጃቸዋለሁ፤ እነርሱንም ብሩ ከታች ሆኖ በድንኳኔ ውስጥ በመሬት ተቀብረዋል።”
ሳኦልም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “አዎ፤ እኔ ኃጢአት ሠርቼአለሁ፤ የእግዚአብሔርን ትእዛዝና አንተ የሰጠኸኝን መመሪያ አልጠበቅሁም፤ ወታደሮቼን በመፍራት እነርሱ የፈለጉትን ሁሉ አደረግሁ፤
ሳኦልም “በእርግጥ በደል ሠርቼአለሁ፤ ይሁን እንጂ ሌላው ቢቀር በሕዝቤ መሪዎችና በእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ፊት አክብረኝ፤ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር እሰግድ ዘንድ ከእኔ ጋር አብረህ ሂድ” ሲል ለመነው።