ኢያሱ 21:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሙሴ አማካይነት እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት የእስራኤል ሕዝብ እነዚህን ከተሞችና የግጦሽ ምድር ለሌዋውያን በዕጣ አካፈሉአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ እስራኤላውያን እግዚአብሔር በሙሴ በኩል ባዘዘው መሠረት፣ እነዚህን ከተሞችና መሰማሪያቸውን ለሌዋውያኑ በዕጣ መደቡላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም በሙሴ አማካይነት እንዳዘዘ የእስራኤል ልጆች እነዚህን ከተሞችና መሰማሪያቸውን ለሌዋውያን በዕጣ ሰጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው የእስራኤል ልጆች እነዚህን ከተሞችና መሰማሪያቸውን ለሌዋውያን በዕጣ ሰጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም በሙሴ እጅ እንዳዘዘ የእስራኤል ልጆች እነዚህን ከተሞችና መሰምርያቸውን ለሌዋውያን በዕጣ ሰጡ። |
እጅግ አስፈሪ የሆነ ቊጣቸው፥ እጅግ ጨካኝ የሆነ መዓታቸው፥ የተረገመ ይሁን። በእስራኤል ምድር ሁሉ እበታትናቸዋለሁ፤ በሕዝቡም መካከል እከፋፍላቸዋለሁ።
ምድሪቱንም በተለያዩት ነገዶችና ጐሣዎች መካከል በዕጣ ተከፋፈሉ፤ የጐሣው ቊጥር ከፍ ላለው ሰፊ መሬት ይሰጠው፤ የጐሣው ቊጥር አነስተኛ ለሆነው ደግሞ ጠበብ ያለ መሬት ይሰጠው። እያንዳንዱ ሁሉ ዕጣው እንደ ወጣለት በዚያ ርስቱ ይሆናል፤ በየአባቶቻችሁ ነገዶች ምድሪቱን በርስትነት ትረከባላችሁ።
ስለዚህም በእግዚአብሔር ትእዛዝ መሠረት የእስራኤል ሕዝብ ለሌዋውያን የሚከተሉትን ከተሞችና ለከብት ግጦሽ የሚሆን መሬት ከርስቶቻቸው ከፍለው ሰጡአቸው።