በዚያም አበኔር ኢያቡስቴን በገለዓድ ግዛቶች፥ በአሴር፥ በኢይዝራኤል፥ በኤፍሬምና በብንያም ይኸውም በመላው እስራኤል ላይ እንዲነግሥ አደረገ።
ኢያሱ 19:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምድሩም ክልል ኢይዝራኤልን፥ ከሱሎትን፥ ሹኔምን፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምድራቸውም የሚከተሉትን ያካትታል፤ ኢይዝራኤል፣ ከስሎት፣ ሱነም፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድንበራቸውም የሚያጠቃልለው ኢይዝራኤልን፥ ከስሎትን፥ ሱነምን፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድንበራቸውም ኢይዝራኤል፥ ከልሰሉት፥ ሱሳን፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድንበራቸውም ወደ ኢይዝራኤል፥ |
በዚያም አበኔር ኢያቡስቴን በገለዓድ ግዛቶች፥ በአሴር፥ በኢይዝራኤል፥ በኤፍሬምና በብንያም ይኸውም በመላው እስራኤል ላይ እንዲነግሥ አደረገ።
አንዲት ቈንጆ ልጃገረድ ለማግኘት በመላው እስራኤል ፍለጋ ተደረገ፤ ሹኔም ተብላ ከምትጠራው ስፍራ አቢሻግ የምትባል አንዲት ልጃገረድ አግኝተው ለንጉሡ አመጡለት፤
እርሱም “ንጉሥ ሰሎሞን አንቺን እምቢ እንደማይልሽ ዐውቃለሁ፤ ስለዚህ አቢሻግ ተብላ የምትጠራውን ሹኔማይት ልጃገረድ በሚስትነት እንዲድርልኝ እባክሽ አማልጅኝ” አላት።
ናቡቴ ተብሎ የሚጠራ አንድ ሰው ነበር፤ እርሱም በኢይዝራኤል በሚገኘው በንጉሥ አክዓብ ቤተ መንግሥት አጠገብ የራሱ ርስት የሆነ አንድ የወይን ተክል ቦታ ነበረው።
አንድ ቀን ኤልሳዕ አንዲት ሀብታም ሴት ወደምትኖርበት ወደ ሱነም ሄደ፤ እርስዋም ምግብ እንዲበላ ጋበዘችው፤ ከዚያን ዕለት ጀምሮ ወደ ሱነም በሚመጣበት ጊዜ ሁሉ በቤትዋ ይመገብ ነበር፤
ኢዮራምም ከንጉሥ ኣዛሄል ጋር ሆኖ በሬማት በተደረገው ጦርነት የደረሰበትን ቊስል ለመፈወስ ወደ ኢይዝራኤል ከተማ ተመለሰ። የአክዓብ ልጅ ኢዮራም በደረሰበት ጒዳት እርሱን ለመጠየቅ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ ሊጠይቀው ወደ ኢይዝራኤል ከተማ ሄደ።
በዚህም ጊዜ ኢዩ ወደ ኢይዝራኤል ደረሰ፤ ኤልዛቤልም ይህን የሆነውን ነገር ሰምታ ዐይንዋን ተኳለች፤ ጠጒርዋንም ተሠርታ በቤተ መንግሥቱ ሰገነት ላይ በመስኮት አዘንብላ ቊልቊል መንገዱን ትመለከት ነበር።
እነርሱም “ኮረብታማይቱ አገር ለእኛ በቂ አይደለችም፤ ከዚህም ሁሉ ጋር በኢይዝራኤል ሸለቆ በቤትሻንና በዙሪያዋ ባሉት ታናናሽ ከተሞችና በሜዳማው አገር የሚኖሩ ከነዓናውያን ብዙ የብረት ሠረገሎች አሉአቸው” ሲሉ መለሱ።