ኢያሱ 12:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢያሱና የእስራኤል ሕዝብ ከዮርዳኖስ በስተምዕራብ ባለው ምድር የነበሩትን ነገሥታት ሁሉ ድል ነሡ፤ ይህም ምድር በሊባኖስ ሸለቆ ከሚገኘው ከባዓልጋድ ተነሥቶ በደቡብ በኩል በኤዶም አጠገብ እስካለው እስከ ሐላክ ተራራ ይደርስ ነበር፤ ኢያሱም ይህን ምድር በማከፋፈል ለእያንዳንዱ ነገድ ርስት አድርጎ ሰጠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ ኢያሱና እስራኤላውያን ከዮርዳኖስ በስተምዕራብ ድል ያደረጓቸው የምድሪቱ ነገሥታት እነዚህ ናቸው፤ ግዛታቸውም በሊባኖስ ሸለቆ ውስጥ ካለው ከበኣልጋድ ተነሥቶ በምዕራብ ሴይር እስካለው እስከ ሐላቅ ተራራ ይደርሳል፤ ኢያሱም የእነዚህን ነገሥታት ምድር እንደ ነገዳቸው አከፋፈል ለእስራኤላውያን በማከፋፈል ርስት አድርጎ ሰጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢያሱና የእስራኤል ልጆች ያሸነፉአቸው የምድሪቱ ነገሥታት እነዚህ ናቸው፤ እነርሱም የነበሩት በዮርዳኖስም ማዶ በምዕራብ በኩል በሊባኖስ ሸለቆ ካለችው ከበኣልጋድ ወደ ሴይር ተራራ እስከሚያወጣው እስከ ሐላቅ ተራራ ድረስ ኢያሱ በየድርሻቸው ርስት አድርጎ ለእስራኤል ነገድ በሰጣት ምድር፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤል ልጆችና ኢያሱ በሊባኖስ ቆላ፥ በበላጋድ ባሕር፥ በዮርዳኖስ ማዶ ወደ ሴይር በሚደርስ በኬልኪ ተራራ የገደሉአቸው የከነዓን ነገሥት እነዚህ ናቸው። ኢያሱም ያችን ምድር ለእስራኤል ወገኖች ሰጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዮርዳኖስም ማዶ በምዕራብ በኩል በሊባኖስ ሸለቆ ካለችው ከበኣልጋድ ወደ ሴይር ተራራ እስከሚያወጣው ወና እስከ ሆነው ተራራ ድረስ ኢያሱ በየክፍላቸው ርስት አድርጎ ለእስራኤል ነገድ በሰጣት ምድር፥ በተራራማው አገር፥ በቈላውም፥ በዓረባም፥ በቁልቁለቱም፥ በምድረ በዳውም፥ በደቡቡም ያሉ ኬጢያውያን አሞራውያንም ከነዓናውያንም ፌርዛውያንም ኤዊያውያንም ኢያቡሳውያንም የሆኑ ኢያሱና የእስራኤል ልጆች የመቱአቸው የምድር ነገሥታት እነዚህ ናቸው፥ |
“እግዚአብሔር በነገረኝ መሠረት ወደ ምድረ በዳ ተመልሰን ወደ ቀይ ባሕር በሚወስደው አቅጣጫ በመጓዝ የኤዶምን ኮረብታማ ቦታ ለብዙ ቀን ዞርን።
ሕዝቡንም እንዲህ ብለህ እዘዝ፤ ዘመዶቻችሁ የዔሳው ዘሮች በሚኖሩበት በኮረብታማው በኤዶም አገር በኩል ታልፋላችሁ፤ እነርሱ እናንተን ይፈሩአችኋል፤ ነገር ግን ተጠንቀቁ፤
እርሱም ወደ ኤዶም ከሚያወጣው ከሐላቅ ተራራ ጀምሮ ከሔርሞን ተራራ በታች እስከ ሊባኖስ ሸለቆ እስከ ባዓልጋድ ድረስ ያሉትን ነገሥታት ሁሉ ማርኮ መታቸው፤ ገደላቸውም፤
እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ኢያሱ ምድሩን ሁሉ በእጁ አደረገ፤ ለእያንዳንዱ ነገድ አንዳንድ ድርሻ ርስት አድርጎ በመስጠት ለእስራኤላውያን በሙሉ አከፋፈለ። ስለዚህም ምድሪቱ ከጦርነት ዐረፈች።
ሕዝቡ በደረቅ ምድር እየተራመዱ በሚሻገሩበት ጊዜ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት የተሸከሙ ካህናት ሕዝቡ ሁሉ ተሻግረው እስካበቁ ድረስ በዮርዳኖስ ወንዝ መካከል በደረቅ ምድር ላይ ቆመው ነበር።
ከዮርዳኖስ ማዶ በተራራማውና በቈላማው አገሮች፥ በሜዲቴራኒያን ባሕር ጠረፍ፥ እስከ ሊባኖስ ድረስ ያሉት የሒታውያን፥ የአሞራውያን፥ የከነዓናውያን፥ የፔሩዛውያን የኤዊያውያንና የኢያቡሳውያን ነገሥታት ይህን በሰሙ ጊዜ፥