Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢያሱ 12:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችና ኢያሱ በሊ​ባ​ኖስ ቆላ፥ በበ​ላ​ጋድ ባሕር፥ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ወደ ሴይር በሚ​ደ​ርስ በኬ​ልኪ ተራራ የገ​ደ​ሉ​አ​ቸው የከ​ነ​ዓን ነገ​ሥት እነ​ዚህ ናቸው። ኢያ​ሱም ያችን ምድር ለእ​ስ​ራ​ኤል ወገ​ኖች ሰጣ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እንግዲህ ኢያሱና እስራኤላውያን ከዮርዳኖስ በስተምዕራብ ድል ያደረጓቸው የምድሪቱ ነገሥታት እነዚህ ናቸው፤ ግዛታቸውም በሊባኖስ ሸለቆ ውስጥ ካለው ከበኣልጋድ ተነሥቶ በምዕራብ ሴይር እስካለው እስከ ሐላቅ ተራራ ይደርሳል፤ ኢያሱም የእነዚህን ነገሥታት ምድር እንደ ነገዳቸው አከፋፈል ለእስራኤላውያን በማከፋፈል ርስት አድርጎ ሰጣቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ኢያሱና የእስራኤል ልጆች ያሸነፉአቸው የምድሪቱ ነገሥታት እነዚህ ናቸው፤ እነርሱም የነበሩት በዮርዳኖስም ማዶ በምዕራብ በኩል በሊባኖስ ሸለቆ ካለችው ከበኣልጋድ ወደ ሴይር ተራራ እስከሚያወጣው እስከ ሐላቅ ተራራ ድረስ ኢያሱ በየድርሻቸው ርስት አድርጎ ለእስራኤል ነገድ በሰጣት ምድር፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ኢያሱና የእስራኤል ሕዝብ ከዮርዳኖስ በስተምዕራብ ባለው ምድር የነበሩትን ነገሥታት ሁሉ ድል ነሡ፤ ይህም ምድር በሊባኖስ ሸለቆ ከሚገኘው ከባዓልጋድ ተነሥቶ በደቡብ በኩል በኤዶም አጠገብ እስካለው እስከ ሐላክ ተራራ ይደርስ ነበር፤ ኢያሱም ይህን ምድር በማከፋፈል ለእያንዳንዱ ነገድ ርስት አድርጎ ሰጠ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7-8 በዮርዳኖስም ማዶ በምዕራብ በኩል በሊባኖስ ሸለቆ ካለችው ከበኣልጋድ ወደ ሴይር ተራራ እስከሚያወጣው ወና እስከ ሆነው ተራራ ድረስ ኢያሱ በየክፍላቸው ርስት አድርጎ ለእስራኤል ነገድ በሰጣት ምድር፥ በተራራማው አገር፥ በቈላውም፥ በዓረባም፥ በቁልቁለቱም፥ በምድረ በዳውም፥ በደቡቡም ያሉ ኬጢያውያን አሞራውያንም ከነዓናውያንም ፌርዛውያንም ኤዊያውያንም ኢያቡሳውያንም የሆኑ ኢያሱና የእስራኤል ልጆች የመቱአቸው የምድር ነገሥታት እነዚህ ናቸው፥

Ver Capítulo Copiar




ኢያሱ 12:7
16 Referencias Cruzadas  

እስከ ሴይ​ርም ከሚ​ያ​ወ​ጣው ከኤ​ኬል ተራራ ጀምሮ ከአ​ር​ሞ​ን​ዔም ተራራ በታች እስከ ሊባ​ኖስ ሜዳና እስከ በላ​ጋድ ድረስ፤ ንጉ​ሦ​ቻ​ቸ​ውን ሁሉ ይዞ መታ​ቸው፤ ገደ​ላ​ቸ​ውም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሙሴ እን​ዳ​ዘ​ዘው ሁሉ ኢያሱ ምድ​ሪ​ቱን ሁሉ ያዘ፤ ኢያ​ሱም ለእ​ስ​ራ​ኤል እንደ ክፍ​ላ​ቸው በየ​ነ​ገ​ዳ​ቸው ርስት አድ​ርጎ ምድ​ሪ​ቱን ሰጣ​ቸው፤ ምድ​ሪ​ቱም ከጦ​ር​ነት ዐረ​ፈች።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በተ​ራ​ራ​ማው በሜ​ዳ​ውም በታ​ላቁ ባሕር ዳር በሊ​ባ​ኖ​ስም ፊት ለፊት የነ​በሩ ነገ​ሥት ሁሉ፥ ኬጤ​ዎ​ና​ዊዉ፥ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊ​ዉም፥ ከነ​ዓ​ና​ዊ​ዉም፥ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ዊ​ዉም፥ ኤዌ​ዎ​ና​ዊ​ዉም፥ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ዉም፥ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ዉም ይህን በሰሙ ጊዜ፥


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት የተ​ሸ​ከሙ ካህ​ናት በዮ​ር​ዳ​ኖስ መካ​ከል በደ​ረቅ መሬት ጸን​ተው ቆመው ነበር፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ፈጽ​መው እስ​ኪ​ሻ​ገሩ ድረስ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ በደ​ረቅ መሬት ተሻ​ገሩ።


ሕዝ​ቡ​ንም እን​ዲህ ብለህ እዘ​ዛ​ቸው፦ በሴ​ይር ላይ በተ​ቀ​መ​ጡት በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ በዔ​ሳው ልጆች ሀገር ታል​ፋ​ላ​ችሁ፤ እነ​ርሱ ይፈ​ሩ​አ​ች​ኋል፤ እን​ግ​ዲህ እጅግ ተጠ​ን​ቀቁ።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዳ​ለኝ ተመ​ል​ሰን በኤ​ር​ትራ ባሕር መን​ገድ ወደ ምድረ በዳ ሄድን፤ የሴ​ይ​ር​ንም ተራራ ብዙ ቀን ዞርን።


ዲሶን መስ​ፍን፥ ኤሶር መስ​ፍን፥ ሪሶን መስ​ፍን፤ በሴ​ይር ምድር በየ​ሹ​መ​ታ​ቸው መሳ​ፍ​ንት የሆኑ የሖሪ መሳ​ፍ​ንት እነ​ዚህ ናቸው።


በዚ​ያች ሀገር የተ​ቀ​መጡ የሖ​ሪ​ያ​ዊው የሴ​ይር ልጆች እነ​ዚህ ናቸው፤ ሉጣን፥ ሦባን፥ ሳባቅ፥ አናም፥


ዔሳ​ውም በሴ​ይር ተራራ ተቀ​መጠ፤ ዔሳ​ውም ኤዶም ነው።


ያዕ​ቆ​ብም ወደ ወን​ድሙ ወደ ዔሳው ወደ ሴይር ምድር ወደ ኤዶም ሀገር በፊቱ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤


በሴ​ይር ተራ​ራ​ዎች ያሉ የኬ​ሬ​ዎስ ሰዎ​ች​ንም በበ​ረሃ አጠ​ገብ እስከ አለ​ችው እስከ ፋራን ዛፍ ድረስ መቱ​አ​ቸው።


እስ​ራ​ኤ​ልን ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ያወጣ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios