ኢያሱ 12:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 ይህም የርስት ድርሻ ኮረብታማውን አገር በስተ ምዕራብ ያለውን የኮረብታ ግርጌ፥ የዮርዳኖስን ሸለቆና በእርሱም ኮረብታዎች ግርጌ ያሉትን በስተ ምሥራቅ በኩል የሚገኘውን ረባዳ ቦታና በደቡብ በኩል የሚገኘውን በረሓማ ምድር ሁሉ ያጠቃልል ነበር፤ ይህም ምድር ቀድሞ የሒታውያን፥ የአሞራውያን፥ የከነዓናውያን፥ የፈሪዛውያን፥ የሒዋውያንና የኢያቡሳውያን መኖሪያ ነበር። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም8 ይህም ተራራማው አገር፤ በስተምዕራብ ያለው የኰረብታ ግርጌ፣ ዓረባ፣ የተራራው ሸንተረሮች፣ ምድረ በዳውና ኔጌብ ማለት የኬጢያውያን፣ የአሞራውያን፣ የከነዓናውያን፣ የፌርዛውያን፣ የኤዊያውያንና የኢያቡሳውያን ምድር ነው። ነገሥታቱም እነዚህ ናቸው፤ Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 በተራራማው አገር፥ በቈላውም፥ በዓረባም፥ በቁልቁለቱም፥ በምድረ በዳውም፥ በደቡቡም ያሉ ኬጢያውያን አሞራውያንም ከነዓናውያንም ፌርዛውያንም ኤዊያውያንም ኢያቡሳውያንም ዘንድ ነበር። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 በተራራና በሜዳ በዓረባ፥ በአሴዶት በቆላው፥ በናጌብ፥ በኬጤዎንና በአሞሬዎን፥ በከናኔዎንና በፌርዜዎን፥ በኢያቡሴዎንና በኤዌዎን ያለ ርስታቸውን አወረሳቸው። Ver Capítulo |