በዚህ ዐይነት የከነዓናውያን ድንበር ከሲዶና አንሥቶ በስተደቡብ በገራር አጠገብ እስካለው እስከ ጋዛ ድረስ፥ በስተ ምሥራቅ እስከ ሰዶም፥ ገሞራ፥ አዳማና በላሻዕ አጠገብ እስካለው እስከ ጸቦይም ድረስ ሆነ።
ኢያሱ 10:41 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢያሱም ከቃዴስ በርኔ እስከ ጋዛ የጎሼንን አካባቢ ሁሉ ጨምሮ፥ እስከ ገባዖን ድረስ ወግቶ ድል አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢያሱም ከቃዴስ በርኔ እስከ ጋዛ እንዲሁም የጎሶምን ምድር ሁሉ እስከ ገባዖን ድረስ በሙሉ ያዘ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢያሱም ከቃዴስ በርኔ እስከ ጋዛ ድረስ የጎሶምንም ምድር ሁሉ እስከ ገባዖን ድረስ መታ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢያሱም ከቃዴስ በርኔ እስከ ጋዛ ድረስ፥ የጎሶምንም ምድር ሁሉ እስከ ገባዖን ድረስ መታ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢያሱም ከቃዴስ በርኔ እስከ ጋዛ ድረስ የጎሶምንም ምድር ሁሉ እስከ ገባዖን ድረስ መታ። |
በዚህ ዐይነት የከነዓናውያን ድንበር ከሲዶና አንሥቶ በስተደቡብ በገራር አጠገብ እስካለው እስከ ጋዛ ድረስ፥ በስተ ምሥራቅ እስከ ሰዶም፥ ገሞራ፥ አዳማና በላሻዕ አጠገብ እስካለው እስከ ጸቦይም ድረስ ሆነ።
የአስቀሎና ከተማ ይህን አይታ ትፈራለች፤ የጋዛ ከተማም ይህን በማየት እጅግ ትጨነቃለች፤ ዔቅሮንም እንዲሁ ተስፋ ትቈርጣለች፤ ጋዛ ንጉሥዋን ታጣለች፤ አስቀሎናም ምድረ በዳ ሆና ትቀራለች።
በፋራን ምድረ በዳ በቃዴስ ወደነበሩት ወደ ሙሴና አሮን ወደ መላውም የእስራኤል ማኅበር መጡ፤ እነርሱም ያዩትን ነገር ሁሉ አስረዱ፤ ያመጡትንም ፍሬ አሳዩአቸው፤
ከዚያም ወደ ዐቅራቢም መተላለፊያ ወደ ደቡብ በማምራት በጺን አልፎ እስከ ቃዴስ በርኔ ይደርሳል፤ ከዚያም በሐጻርአዳር ሰሜናዊ ምዕራብ አልፎ እስከ ዓጽሞን ይደርሳል።
“ከዚያም እግዚአብሔር አምላካችን እንዳዘዘን ከሲና ተነሥተን እናንተ ባያችሁት አስቸጋሪ በረሓ በተራራማው በአሞራውያን አገር በኩል አድርገን ወደ ቃዴስ በርኔ መጣን።
እግዚአብሔር፥ ‘ሂዱ፤ የሰጠኋችሁንም የተስፋ ምድር ውረሱ’ ብሎ ከቃዴስ በርኔ በላካችሁም ጊዜ በእርሱ ላይ ዐመፃችሁ እንጂ አልተማመናችሁበትም፤ ለቃሉም አልታዘዛችሁም።
እግዚአብሔር አሞራውያንን ለእስራኤላውያን አሳልፎ በሰጠበት ቀን ኢያሱ ከእግዚአብሔር ጋር ተነጋገረ፤ እርሱም በእስራኤል ፊት እንዲህ አለ፦ “ፀሐይ በገባዖን፥ ጨረቃም በኤሎን ሸለቆ ላይ ይቁሙ” አለ።
ገባዖን በነገሥታት እንደሚተዳደሩት ከተሞች ትልቅና ከዐይ ትበልጥ የነበረች ከተማ ከመሆንዋም በላይ ሰዎችዋም ብርቱ ጦረኞች ስለ ነበሩ፥ አዶኒጼዴቅ በጣም ፈራ።
ኢያሱ እነዚያን አገሮች፦ ተራራማውን፥ ኔጌብን፥ የጎሼንን ምድር፥ ቈላማውን፥ የዮርዳኖስን ሸለቆ፥ ቈላማውንና ደጋማውን የእስራኤልን ምድር ሁሉ ያዘ።
አንድ ቀን ሶምሶን የፍልስጥኤማውያን ከተማ ወደሆነችው ወደ ጋዛ ሄደ፤ እዚያም አንዲት አመንዝራ ሴት አይቶ ከእርስዋ ጋር ለማደር ወደ ቤትዋ ገባ፤
ፍልስጥኤማውያንም ከማረኩት በኋላ ሁለቱን ዐይኖቹን አወጡ፤ ወደ ጋዛም ወስደው በነሐስ ሰንሰለት በማሰር በታሰረበት ቤት እህል እንዲፈጭ አደረጉት፤
ስለ በደላቸው የሚከፈሉ ስጦታዎች ይሆኑ ዘንድ ፍልስጥኤማውያን ለእግዚአብሔር የላኩአቸው በእባጮች አምሳል የተሠሩ አምስት የወርቅ እንክብሎች አሽዶድ፥ ጋዛ፥ አስቀሎና፥ ጋትና ዔቅሮን ተብለው በሚጠሩት ከተሞቻቸው ስም የተላኩ ነበሩ፤