ኢያሱ 10:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ቀን ኢያሱ ማቄዳን ያዘ፤ ንጉሥዋንም በሰይፍ ገደለ፤ በከተማይቱ የነበሩትን ሰዎች ሁሉ አንድም ሳያስቀር ፈጀ፤ በማቄዳም ንጉሥ ላይ ያደረገው ቀድሞ በኢያሪኮ ንጉሥ ላይ ባደረገው ዐይነት ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያች ዕለት ኢያሱ መቄዳን ያዘ፤ ከተማዪቱንና ንጉሧንም በሰይፍ ስለት መታ፤ አንድም ሰው ሳያስቀር በውስጧ ያለውን ሁሉ ፈጽሞ ደመሰሰ፤ በኢያሪኮ ንጉሥ ላይ ያደረገውንም ሁሉ፣ በመቄዳ ንጉሥ ላይ አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም ቀን ኢያሱ መቄዳን ያዛት፥ እርሷንና ንጉሥዋንም በሰይፍ ስለት መታ፤ በእርሷም ያሉትን ሰዎች ሁሉ ፈጽሞ አጠፋቸው፥ ከእነርሱም አንድም እንኳ አላስቀረም፤ በኢያሪኮም ንጉሥ ላይ እንዳደረገው እንዲሁ በመቄዳ ንጉሥ ላይ አደረገ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ቀን መቄዳን ያዟት፤ እርስዋንና ንጉሥዋንም በሰይፍ ስለት ገደሉ፤ በእርስዋም ያሉትን ነፍሳት ሁሉ ፈጽመው አጠፉአቸው፤ ከእነርሱም አንዱን ስንኳ አላስቀሩም፤ የዳነም፥ ያመለጠም የለም፤ በኢያሪኮም ንጉሥ እንዳደረጉ በመቄዳ ንጉሥ አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ቀን ኢያሱ መቄዳን ያዛት፥ እርስዋንና ንጉሥዋንም በሰይፍ ስለት መታ፥ በእርስዋም ያሉትን ነፍሳት ሁሉ ፈጽሞ አጠፋቸው፥ ከእነርሱም አንዱን ስንኳ አላስቀረም፥ በኢያሪኮም ንጉሥ እንዳደረገ በመቄዳ ንጉስ አደረገ። |
ወዲያውም እያንዳንዱን ከተማ ወረን አቃጠልነው፤ በነዚያ ከተሞች የነበሩትንም ሰዎች ወንዶችንና ሴቶችን፥ ሕፃናትንም ጭምር አንድ እንኳ በሕይወት ሳናስቀር ሁሉንም ደመሰስን።
እግዚአብሔር አምላክህ እነዚህን ሁሉ ሕዝቦች ለእናንተ አሳልፎ ሲሰጣቸውና እነርሱን ድል በምትነሣበት ጊዜ ሁሉንም መደምሰስ አለብህ፤ ከእነርሱ ጋር ምንም ዐይነት ውል አታድርግ፤ አትራራላቸውም።
እግዚአብሔርም በርስዋና በንጉሥዋ በእስራኤል ላይ ለእስራኤላውያን ድልን ሰጣቸው፤ ኢያሱም ከተማይቱንና በእርስዋ ያሉትን ሰዎች አጠፋ፤ በንጉሥዋም ላይ በኢያሪኮ ንጉሥ ላይ እንዳደረገው አደረገበት።
እግዚአብሔርም ጦርነቱ በተጀመረ በሁለተኛው ቀን ለእስራኤላውያን በላኪሽ ላይ ድልን ሰጣቸው፤ በሊብና ባደረጉትም ዐይነት በከተማይቱ ያገኙትን ሰው ሁሉ በሰይፍ ፈጁ፤
እርስዋንም ይዘው ንጉሡን፥ በከተማይቱና በአካባቢዋም የገጠር ከተሞች ያገኙትን ሁሉ ገደሉ፤ ኢያሱም ልክ በዔግሎን ባደረገው ዐይነት ከተማይቱ እንድትደመሰስ ፈረደባት፤ በእርስዋም ውስጥ በሕይወት የተረፈ አንድም አልነበረም።
ንጉሡንና ከተማዎቹን ሁሉ ያዙ፤ የከተማዎቹንም ሰዎች በሰይፍ ፈጁ፤ ልክ በኬብሮን፥ በሊብናና በነገሥታቱ ላይ እንዳደረጉት በዶቢርም አንድ ሰው እንኳ ሳይተርፋቸው በዚያ ያሉትን ሰዎች ሁሉ ፈጁ።
ገዴሮት፥ ቤትዳጎን፥ ናዕማና ማቄዳ ተብለው የሚጠሩ በድምሩ ዐሥራ ስድስት ከተሞች ሲሆኑ በዙሪያቸው ያሉትን ታናናሽ ከተሞችን ሁሉ ያጠቃልላል።
ከዚህ በፊት በኢያሪኮና በንጉሥዋ ላይ የደረሰውን ጥፋት በዐይና በንጉሥዋም ላይ ደግሞ ትፈጽምባቸዋለህ፤ ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ ከእርስዋ የሚገኘውን የንብረትና የከብት ምርኮ ለራሳችሁ ታደርጋላችሁ፤ ከኋላ በኩል በከተማይቱ ላይ በድንገት አደጋ ለመጣል ተዘጋጅ።”