ዮሐንስ 3:35 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አብ ልጁን ይወዳል፤ ሁሉንም ነገር በእጁ አስረክቦታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አብ ወልድን ይወድዳል፤ ሁሉንም ነገር በእጁ ሰጥቶታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አባት ልጁን ይወዳል፥ ሁሉንም በእጁ ሰጥቶታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብ ልጁን ይወዳልና፥ ሁሉን በእጁ ሰጠው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አባት ልጁን ይወዳል ሁሉንም በእጁ ሰጥቶታል። |
ራብ በመላው ግብጽ ምድር እየተስፋፋ በሄደ ጊዜ፥ ሕዝቡ ወደ ፈርዖን ሄዶ “ምግብ ስጠን!” ብሎ ጮኸ። ፈርዖንም “ወደ ዮሴፍ ሂዱና እርሱ የሚላችሁን አድርጉ” ብሎ አዘዛቸው።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔ የምደግፈው የመረጥኩትና በእርሱም ደስ የሚለኝ አገልጋዬ ይህ ነው፤ መንፈሴ በእርሱ እንዲያድርበት አደርጋለሁ፤ እርሱ ለሕዝቦች ሁሉ ትክክለኛ ፍርድን ያመጣል።
በልዩ ልዩ አገር የሚኖሩ ሕዝቦችና ልዩ ልዩ ቋንቋ የሚናገሩ ነገዶች ያገለግሉት ዘንድ ሥልጣን፥ ክብርና ንጉሥነት ተሰጠው፤ ግዛቱም የማይጠፋ ዘለዓለማዊ ነው፤ ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም።
አባቴ ሁሉን ነገር ሰጥቶኛል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ ማንም የለም። እንዲሁም ከወልድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም፤ ማንም ወልድ ካልገለጠለት በቀር አብን ሊያውቅ አይችልም።
ጴጥሮስ ገና ይህን ሲናገር ሳለ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፤ ከደመናውም ውስጥ “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት!” የሚል ድምፅ መጣ።
“ሁሉ ነገር ከአባቴ ተሰጥቶኛል፤ ወልድ ማን መሆኑን ከአብ በቀር ማንም የሚያውቅ የለም፤ እንዲሁም አብ ማን መሆኑን ከወልድ በቀር ወይም ወልድ ሊገልጥለት ከሚፈቅድለት ሰው በቀር ሌላ ማንም የሚያውቅ የለም።”
እኔ የምለምነው እኔ በእነርሱ አንተም በእኔ እንደ ሆንክ እነርሱም በፍጹም አንድ እንዲሆኑ ነው፤ እንዲሁም እኔን እንደ ላክኸኝና እኔን በወደድከኝ መጠን እነርሱንም እንደ ወደድካቸው ዓለም እንዲያውቅ ነው።
አንተ እኔን የወደድክበት ፍቅር በእነርሱ ላይ እንዲሆንና እኔም በእነርሱ እንድሆን እነርሱ አንተን እንዲያውቁ አድርጌአለሁ፤ ደግሞም እንዲያውቁ አደርጋቸዋለሁ።”
“እግዚአብሔር ሁሉን ነገር በሥልጣኑ ሥር አድርጎለታል” የሚል ተጽፎአል፤ ነገር ግን “ሁሉ ነገር በሥልጣኑ ሥር ሆኖአል” ሲባል ሁሉን ነገር በሥልጣኑ ሥር ያደረገለትን እግዚአብሔር አብን አይጨምርም።
አሁን ግን በእነዚህ በኋለኞቹ ዘመናት ሁሉን ነገር ወራሽ ባደረገው በልጁ አማካይነት ለእኛ ተናገረን፤ ዓለምንም ሁሉ የፈጠረው በእርሱ ነው።