ዮሐንስ 21:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ጊዜ ኢየሱስ የሚወድደው ደቀ መዝሙር ጴጥሮስን “ጌታ ነው እኮ!” አለው። ስምዖን ጴጥሮስ “ጌታ ነው” ማለትን በሰማ ጊዜ ለሥራ ብሎ ልብሱን አውልቆ ስለ ነበረ ወዲያው ልብሱን ለበሰና ወደ ባሕሩ ዘሎ ገባ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስ ይወድደው የነበረው ደቀ መዝሙርም፣ ጴጥሮስን፣ “ጌታ እኮ ነው!” አለው። ስምዖን ጴጥሮስም፣ “ጌታ እኮ ነው!” የሚለውን ቃል በሰማ ጊዜ፣ አውልቆት የነበረውን መደረቢያ ልብስ ታጠቀና ዘልሎ ወደ ባሕሩ ገባ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስ ይወደው የነበረውም ደቀመዝሙር ጴጥሮስን “ጌታ እኮ ነው” አለው። ስምዖን ጴጥሮስም ጌታ መሆኑን በሰማ ጊዜ ዕራቁቱን ነበረና ልብሱን ታጥቆ ወደ ባሕር ዘለለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታችን ኢየሱስ ይወደው የነበረ ያ ደቀ መዝሙርም ለጴጥሮስ፥ “ጌታችን ነው እኮ” አለው፤ ስምዖን ጴጥሮስም ጌታችን እንደ ሆነ በሰማ ጊዜ የሚለብሰውን ልብስ አንሥቶ በወገቡ ታጠቀ፤ ራቁቱን ነበርና ወደ ባሕር ተወረወረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስ ይወደው የነበረውም ደቀ መዝሙር ጴጥሮስን፦ “ጌታ እኮ ነው” አለው። ስለዚህ ስምዖን ጴጥሮስ ጌታ መሆኑን በሰማ ጊዜ ዕራቁቱን ነበረና ልብሱን ታጥቆ ወደ ባሕር ራሱን ጣለ። |
የውሃ ብዛት የፍቅርን እሳት ሊያጠፋ አይችልም፤ ጐርፍም ጠራርጎ ሊወስዳት አይችልም፤ ሰው ባለው ሀብት ሁሉ ፍቅርን ለመግዛት ቢሞክር ፍቅር በገንዘብ ስለማትገኝ ሰዎች ይዘባበቱበታል።
ስለዚህ እርስዋ ወደ ስምዖን ጴጥሮስና ኢየሱስ ወደሚወደው ወደ ሌላው ደቀ መዝሙር እየሮጠች ሄደችና “ጌታን ከመቃብሩ አውጥተው ወስደውታል፤ የት እንዳኖሩት አናውቅም” አለቻቸው።
ጴጥሮስ ዘወር ብሎ ኢየሱስ የሚወድደው ደቀ መዝሙር ሲከተለው አየ፤ ይህ ደቀ መዝሙር በእራት ጊዜ ወደ ኢየሱስ ተጠግቶ፥ “ጌታ ሆይ፥ አሳልፎ የሚሰጥህ ማን ነው?” ብሎ የጠየቀው ነው።
እግዚአብሔር ለእስራኤል ሕዝብ ቃሉን መላኩ የታወቀ ነው፤ በሁሉ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ሰላምን እየሰበከ የመጣውም ለእነርሱ ነው።