Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዮሐንስ 20:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ይህንንም ብሎ እጆቹንና ጐኑን አሳያቸው፤ ደቀ መዛሙርቱም ጌታን ባዩ ጊዜ ደስ አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ይህንም ብሎ እጆቹንና ጐኑን አሳያቸው፤ ደቀ መዛሙርትም ጌታን ባዩት ጊዜ እጅግ ደስ አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ይህንንም ብሎ እጆቹንም ጎኑንም አሳያቸው። ደቀ መዛሙርቱም ጌታን ባዩ ጊዜ ደስ አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ይህ​ንም ብሎ እጆ​ቹ​ንና ጎኑን አሳ​ያ​ቸው፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ጌታ​ች​ንን ባዩት ጊዜ ደስ አላ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ይህንም ብሎ እጆቹንም ጎኑንም አሳያቸው። ደቀ መዛሙርቱም ጌታን ባዩ ጊዜ ደስ አላቸው።

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 20:20
9 Referencias Cruzadas  

እንዲሁም እናንተ አሁን ታዝናላችሁ፤ ነገር ግን እኔ እንደገና አያችኋለሁ፤ ልባችሁም ደስ ይለዋል፤ ደስታችሁንም የሚወስድባችሁ የለም።


ከመጀመሪያው ስለ ነበረው ስለ ሕይወት ቃል እንጽፍላችኋለን፤ ይህ የሕይወት ቃል የሰማነውና በዐይኖቻችን ያየነው፥ የተመለከትነውና በእጆቻችን የዳሰስነው ነው።


ከዚህ በኋላ ቶማስን፥ “ጣትህን ወዲህ አምጣና እጆቼን እይ፤ እጅህንም አምጣና በጐኔ ውስጥ አግባው፤ እመን እንጂ እምነተ ቢስ አትሁን” አለው።


እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ እናንተ ታለቅሳላችሁ፤ ትጮኻላችሁም፤ ዓለም ግን ደስ ይለዋል፤ እናንተ ታዝናላችሁ፤ ነገር ግን ሐዘናችሁ ወደ ደስታ ይለወጣል።


ነገር ግን ከወታደሮቹ አንዱ፥ ጐኑን በጦር ወጋው፤ ወዲያውኑ ከጐኑ ደምና ውሃ ወጣ።


ከዚህ በኋላ ሴቶቹ በፍርሃትና በታላቅ ደስታ ከመቃብሩ በፍጥነት ሄዱ፤ ለደቀ መዛሙርቱም ሊነግሩ ሮጡ።


ስለዚህ ሌሎች ደቀ መዛሙርት ቶማስን “ጌታን አየነው” አሉት። እርሱ ግን “በምስማር የተወጉትን እጆቹን ካላየሁና ጣቴን በምስማር በተወጋው ውስጥ ካላገባሁ፥ እጄንም በጐኑ ቊስል ካላገባሁ አላምንም” አላቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios