ዮሐንስ 19:34 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ከወታደሮቹ አንዱ፥ ጐኑን በጦር ወጋው፤ ወዲያውኑ ከጐኑ ደምና ውሃ ወጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ከወታደሮቹ አንዱ የኢየሱስን ጐን በጦር ወጋው፤ ወዲያውም ደምና ውሃ ፈሰሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ከወታደሮቹ አንዱ ጎኑን በጦር ወጋው፤ ወዲያውም ደምና ውሃ ወጣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ከጭፍሮቹ አንዱ የቀኝ ጎኑን በጦር ወጋው፤ ያንጊዜም ከእርሱ ደምና ውኃ ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ከጭፍሮች አንዱ ጎኑን በጦር ወጋው፤ ወዲያውም ደምና ውኃ ወጣ። |
“በዚያን ጊዜ በዳዊት ዘሮችና በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ላይ የርኅራኄና የጸሎት መንፈስ እሞላለሁ፤ ይህንንም የማደርገው እነርሱ ለአንድያ ልጅና ለበኲር ልጅ እንደሚለቀስ ለወጉት ምርር ብለው እንዲያለቅሱለት ነው።
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “በዚያን ጊዜ ለዳዊት ልጆችና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ከኃጢአታቸውና ከርኲሰታቸው የሚያነጻ ምንጭ ይከፈታል።
እናንተን ግን እግዚአብሔር ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ አደረገ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን ጥበባችን፥ ጽድቃችን፥ ቅድስናችንና ቤዛችን እንዲሆን አደረገው።
ከእናንተም አንዳንዶቻችሁ እንዲሁ ነበራችሁ፤ አሁን ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስምና በአምላካችን መንፈስ ከኃጢአት ታጥባችኋል፤ ለእግዚአብሔር የተለየ ቅዱስ ሕዝብ ሆናችኋል፤ ጸድቃችኋልም።
ክርስቶስ ከዐመፃ ሁሉ ሊያድነንና መልካም ሥራ ለመሥራት ትጉሆችና ለእርሱ የተለየን ንጹሕ ሕዝብ እንድንሆን ያነጻን ዘንድ ስለ እኛ ራሱን አሳልፎ ሰጠ።
ይህም ውሃ አሁን እናንተን የሚያድን የጥምቀት ምሳሌ ነው፤ ይህ ጥምቀት የሰውነትን ዕድፍ ማስወገድ ሳይሆን ንጹሕ ኅሊናን ለማግኘት ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብ ልመና ነው፤ የሚያድናችሁም በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ አማካይነት ነው፤
ጥምቀቱን በሚያመለክት ውሃና ሞቱን በሚያመለክት ደም የመጣው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ የመጣው በውሃ ብቻ ሳይሆን በውሃና በደም ነው። ይህም እውነት ስለ ሆነ ይህ ነገር እውነት መሆኑን መንፈስ ቅዱስ ይመሰክራል፤
እኔም “ጌታ ሆይ፥ አንተ ታውቃለህ” አልኩት። እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “እነዚህ ታላቁን መከራ አልፈው የመጡ ናቸው፤ ልብሳቸውንም በበጉ ደም አጥበው ነጭ አድርገውታል፤