ዮሐንስ 15:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ መረጥኳችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ ሄዳችሁ ብዙ ፍሬ እንድታፈሩ፥ ፍሬአችሁም ነዋሪ እንዲሆን ሾምኳችሁ። ስለዚህ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አብ ይሰጣችኋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ እንድትሄዱና ፍሬ እንድታፈሩ፣ ፍሬያችሁም እንዲኖር ሾምኋችሁ። ስለዚህም አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ አብም በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ እንደሚሰጣችሁ፥ እንድትሄዱና ፍሬ እንድታፈሩ ፍሬአችሁም እንዲኖር ሾምኋችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ የመረጣችሁኝ አይደለም፤ እንድትሄዱ፥ ፍሬም እንድታፈሩ፥ ፍሬአችሁም እንዲኖር፤ አብንም በስሜ የምትለምኑት ነገር ቢኖር ሁሉን እንዲሰጣችሁ ሾምኋችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ አብም በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ እንዲሰጣችሁ፥ ልትሄዱና ፍሬ ልታፈሩ ፍሬአችሁም ሊኖር ሾምኋችሁ። |
ከሞት የተረፉትም የእስራኤል ሕዝብ በብዙ ሕዝቦች መካከል እግዚአብሔር እንደሚልከው ጠልና በሣር እንደሚወርድ ካፊያ ይሆናሉ፤ ተማምነው የሚጠባበቁት ሰውን ሳይሆን እግዚአብሔርን ብቻ ይሆናል።
ይህን የምናገረው ስለ ሁላችሁም አይደለም፤ እኔ የመረጥኳችሁን ዐውቃለሁ፤ ነገር ግን ‘እንጀራዬን የበላ በእኔ ላይ በጠላትነት ተነሣብኝ’ የሚለው የቅዱስ መጽሐፍ ቃል መፈጸም አለበት።
የዓለም ብትሆኑ ዓለም የራሱ የሆነውን በወደደ ነበር፤ ነገር ግን የዓለም ስላልሆናችሁና እኔ ከዓለም ለይቼ ስለ መረጥኳችሁ፥ ዓለም ይጠላችኋል።
“እኔ የወይን ግንድ ነኝ፤ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ፤ ብዙ ፍሬ የሚያፈራው በእኔ የሚኖርና እኔም በእርሱ የምኖርበት ነው፤ ነገር ግን ያለ እኔ ምንም ማድረግ አትችሉም።
ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኀይልን ትቀበላላችሁ፤ በዚያን ጊዜ በኢየሩሳሌም፥ በይሁዳ ምድር ሁሉ፥ በሰማርያ፥ እስከ ምድርም ዳርቻ ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ።”
የተገለጠውም አስቀድሞ በእግዚአብሔር ለተመረጡት ምስክሮች ነው እንጂ ለሕዝቡ ሁሉ አይደለም፤ እርሱ ከሞት ከተነሣ በኋላ እኛ ከእርሱ ጋር አብረን የበላንና የጠጣን ምስክሮቹ ነን፤
ጌታም ሐናንያን እንዲህ አለው፦ “እርሱ ስሜን ለአረማውያን፥ ለነገሥታትና ለእስራኤል ሰዎች የሚያሳውቅ፥ የእኔ ምርጥ መሣሪያ ስለ ሆነ ወደ እርሱ ሂድ፤
ወንድሞቼ ሆይ! በሌሎች አሕዛብ መካከል ብዙ አማኞችን እንዳገኘሁ እንዲሁም በእናንተ መካከል አማኞችን ለማግኘት ፈልጌ ነበር፤ ነገር ግን ወደ እናንተ ለመምጣት ብዙ ጊዜ ዐቅጄ እስከ አሁን ያልተሳካልኝ መሆኑን እንድታውቁ እወዳለሁ።
ይህ ሁሉ ነገር የደረሰባቸው ለእኛ የማስጠንቀቂያ ምሳሌ እንዲሆን ነው፤ የተጻፈውም በዘመናት መጨረሻ ላይ ለምንገኘው ለእኛ ትምህርት እንዲሆነን ነው።
እኛ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጃቸውን መልካም ሥራዎች እንድንሠራ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት እንደገና የተፈጠርን የእግዚአብሔር ፍጡሮች ነን።
ይህም የሚሆነው ተመሥርታችሁና ተደላድላችሁ በወንጌሉ ከተገኘው ተስፋ ሳትናወጡ በእምነት ጸንታችሁ ስትኖሩ ብቻ ነው፤ ይህም ወንጌል እናንተ የሰማችሁትና በዓለም ላይ ላሉት ሰዎች ሁሉ የተሰበከ ነው፤ እኔ ጳውሎስም አገልጋይ የሆንኩት ለዚሁ ወንጌል ነው።
እናንተ ወንጌልን ከሰማችሁበትና የእግዚአብሔርንም ጸጋ እውነተኛነት ከተረዳችሁበት ቀን ጀምሮ ይህ ወንጌል በእናንተ መካከል እንደሆነው በመላው ዓለም በማፍራትና በማደግ ላይ ነው።
እኔም እምነትንና እውነትን ለማብሠር ሐዋርያና አስተማሪ ሆኜ ወደ አሕዛብ የተላክሁት በዚህ ምክንያት ነው፤ ይህንንም ስል እውነት እናገራለሁ እንጂ አልዋሽም።
አንተን በቀርጤስ የተውኩበት ምክንያት ያልተስተካከለውን እንድታስተካክልና ባዘዝኩህም መሠረት የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎችን በየከተማው እንድትሾም ነው።
አቤል ከቃየል መሥዋዕት የበለጠውን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ያቀረበው በእምነት ነው፤ እግዚአብሔር የአቤልን መባ በደስታ በተቀበለ ጊዜ አቤል በእምነቱ ጻድቅ መሆኑ ተመሰከረለት፤ አቤል ቢሞትም እንኳ በእምነቱ አማካይነት አሁንም እየተናገረ ነው።
ጌታ ክርስቶስን በልባችሁ አክብሩት፤ ለሕይወታችሁም ጌታ አድርጉት፤ በእናንተ ስላለውም ተስፋ ለሚጠይቃችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ሁልጊዜ ዝግጁዎች ሁኑ።
ፍቅር ማለት እንዲህ ነው፤ እኛ እግዚአብሔርን ስለ ወደድነው ሳይሆን እርሱ ስለ ወደደንና ኃጢአታችንን እንዲደመስስ ልጁን ስለ ላከልን ነው።